Kishore Kumar Hits

Tsehaye Yohannes - Yamelake Sera lyrics

Artist: Tsehaye Yohannes

album: Letinish


የእምነት ማህተብ የማንነት የጥቁሮች አሻራ
የሰንደቆች ሁሉ ሰንደቅ የነፃነት አውራ
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የአምላክ እጅ ስራ
የእምነት ማህተብ የማንነት የጥቁሮች አሻራ
የሰንደቆች ሁሉ ሰንደቅ የነፃነት አውራ
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የአምላክ እጅ ስራ
የነፃነት መታወቂያ
የአለም ምሳሌ ትኩረት
በድል ሰገነት ይዋባል
በአእዋፍ ዜማ ድምቀት
የቸር የጀግና የጨዋ
የአትንኩኝ ባይ ህዝብ አርማ
የሀበሻ ምድር መለዮ
የጥቁር አውደ ግርማ
የኢትዮጵያ የምነት ማህተብ የማንነት የጥቁሮች አሻራ
የሰንደቆች ሁሉ ሰንደቅ የነፃነት አውራ
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የአምላክ እጅ ስራ
የአንድነት ፍቅር ትስስር ጋሻችን
የኛነታችን አለኝታ ፋናችን
እንዲህ ደርጅቶ የፈራው ፀጋችን
ይከበር እንዲያስከብረን አርማችን
በአርበኞች ደም የሚያበራው የትውልድ አደራው
ይከበር ባንዲራው
ወድቆ በደም በተነሳው አረ በባንዲራው
ይጠበቅ አደራው
በጀግኖችሽ እልፈት ፀንቶ
ታሪክ ሰርቶ ቢናፍቅም
የቆየልን ለዘመናት
የሰንደቆች ሁሉ ኩራት
የእምነት ማህተብ የማንነት የጥቁሮች አሻራ
የሰንደቆች ሁሉ ሰንደቅ የነፃነት አውራ
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የአምላክ እጅ ስራ
የብሩክ ምድር ፈርጥ
የነገስታት ማጌጫ
የአንበሶች አጥር ምልክት
የአፍሪካ ቀለም ማውጫ
ከቀስተደመናው ፈልቆ
ከቅዱስ ቃል በረከት
የክቡር ኑዛዜ ሚስጥር
የቃልኪዳኑን ጥልቀት
የኢትዮጵያዊ የምነነት ማህተብ የማንነት የጥቁሮች አሻራ
የሰንደቆች ሁሉ ሰንደቅ የነፃነት አውራ
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የአምላክ እጅ ስራ
በአለም ጉባዔ የኖረ በድምቀት
ህዋውን ጥሶ ያለፈ በኩራት
በልጆችሽ ደም አጥንት ይኖራል
ዘልዓለም በክብር ስፍራ ያበራል
በአርበኞች ደም የሚያበራው የትውልድ አደራው
ይከበር ባንዲራው
ወድቆ በደም በተነሳው አረ በባንዲራው
ይጠበቅ አደራው
ተከባብረው መስጊድ ታቦት
በባንዲራው ግርሚዊነት
በህብር ቀለም አሸብርቆ
በአደባባይ ታየ ደምቆ
በአርበኞች ደም የሚያበራው የትውልድ አደራው
ይከበር ባንዲራው
ወድቆ በደም በተነሳው አረ በባንዲራው
ይጠበቅ አደራው
ተከባብረው መስጊድ ታቦት
በባንዲራው ግርሚዊነት
በህብር ቀለም አሸብርቆ
በአደባባይ ታየ ደምቆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists