Kishore Kumar Hits

Tsehaye Yohannes - Yetnebersh lyrics

Artist: Tsehaye Yohannes

album: Yalanchema


ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ
ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ
እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ
አፍቅሬህ ኖራለው ስትይኝ ከርመሻል
ታምኜ ዘልቃለው ስትይኝ ከርመሻል
ያኔ ባንደበትሽ ፅኑ ሰው መስለሻል
ቃልሽ የታጠፈው ዛሬ ምን ነክቶሻል
ከአካሌ መለየት መራቁን ስትመርጪ
ሸርተት እያልሽብኝ ከእቅፌ ስትወጪ
ልቤን እየከፋው ላሰናብትሽ እንጂ
ትከትዬ አልመጣም ጥለሺኝ ስትሄጂ
በደል ያሻከረው ሆዴን ላታባቢ
የጨከነ አንጀቴን ችለሽ ላታባቢ
የማይሽር ጥላቻን በኔ ልብ አፍርተሽ
በእምባ መማፀኑን አታስቢ ደፍረሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ
ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ
እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ
እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ
ስታጠፊ ኖረሽ ስታገስሽ ኖሬ
ስንቱን ጊዜ አለፍኩት ቀን በቀን መክሬ
ያንቺ ነገር ባይሆን እየፈጩ ጥሬ
ደክሜልሽ ነበር እኔስ እስከዛሬ
በእድሜ ሳይገደብ ከልጅ እስከ አዋቂ
የበደለ ሰው ነው ይቅርታ ጠያቂ
መቻሌ ሳያንሰኝ የጥፋትሽ ህመም
እንደው ምን አርጌሽ ይቅር በይኝ ልበል
ዛሬ ህሊናሽ ወቅሶሽ ምንም ብትቆጪ
በደልሽ አጥሮሻል መቼም ከኔ አትመጪ
የፀፀት መንገዱን ጎዳናው ከታየሽ
ምህረት ባልነፍግሽም አንቺ ግን ዘገየሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ
የት ነበርሽ የት ነበርሽ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists