Kishore Kumar Hits

Jah Lude - Inde Isachew lyrics

Artist: Jah Lude

album: Yachin Neger


ገና በእንጭጭ ዘመን አብሮኝ ባለዉ
ቅን መልካም ያለዉ ምክሮቻቸዉ
ሳያደርገኝ እኔን መካሪ አልባ
ለወግ በቃሁ ዛሬ በአባባ
ትዝ የሚለኝ ጫካዉ ዛፎች ስር ስር
ሰዉ በሌለበት በዚያ በዱር
በጨቅላነት ዕድሜ ሰዉ ፍለጋ
ሳልፈራ ዱር ሄጄ አባባ ጋ
ያኔም ባሉኝ ነበር ዛሬ
ማፈሬም ሰዎችን ማፍቀሬ
በመልካም ላይ ለቆምኩበት
የእሳቸዉም ድርሻ አለበት
ያኔም ባሉኝ ነበር ዛሬ
ማፈሬም ሰዎችን ማፍቀሬ
በመልካም ላይ ለቆምኩበት
አባባም ድርሻቸዉ አለበት
እንደ እሳቸዉ እንደ እሳቸዉ
እንደ እሳቸዉ እንደ እሳቸዉ
ባልኖርም ዘመን አቋቋሜ
መራራ እንዳልሆን ዉስጤም ደሜ
ቀድሞም ለካ ፊቴን በመመልከት
የደጋጎች ናት አዉ ህይወት
በየህዝቦቹም ዉስጥ መልካም ስራ
ሰርቼ እንደእርሳቸዉ ልጠራ
ምክር አድማጭ ህብረት ወዳጅ
መልካም ሁሉም ያላቸዉ ወዳጅ
ከምድር ኑሮ ስም እንዲረባ
ይሄዉ መች ቆዩበት አባባ
ሀብቱስ እድሜን መች ሰጣቸዉ
በምድር ቀረ እንጂ ምግባራቸዉ
ከምድር ኑሮ ስም እንዲረባ
ይሄዉ መች ቆዩበት አባባ
ሀብቱስ እድሜን መች ሰጣቸዉ
በምድር ቀረ እንጂ ምግባራቸዉ
እንደ እሳቸዉ እንደ እሳቸዉ
እንደ እሳቸዉ እንደ እሳቸዉ
እንደ እሳቸዉ እንደ እሳቸዉ
እንደ እሳቸዉ እንደ እሳቸዉ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists