Kishore Kumar Hits

Gossaye Tesfaye - Dagna Dagna lyrics

Artist: Gossaye Tesfaye

album: Siyamish Yamegnal


እሷን ለኔ ብቻ ፈጥሯት
ከሩቅ ያየ መች አውቋት
ይሁን ማንም አይረዳት የልቤን ኩራት
አጋዥ አልፈልግም እኔ አለሁላት
እኔ እወራረዳለሁ በእሷ ቁሜ ልሟገት
ጨዋ ደግ ያፈራት ቆንጆ ልበ ሙሉ ናት
እኔ ወደድኳት ልበ ሙሉ ናት

ጠቢብ ያልደፈራት ያላያት ቅኔ
ሰው ቢጥል ቢያነሳት የማውቃት እኔ
እስቲ በል ፈትኑኝ በቃሌ ልፈር (ልፈር)
እኔ የማላውቀው ቢኖራት ነገር
በእሷ ካፈርኩኝ ይፈረደኛ
ዳኛ ዳኛ የቀዬው ዳኛ
ከተረታሁ ይፍረድብኛ
አፍሬ በእሷ ባጥፍ ምላሴን
ንብረቴን ልጣ ሰንጋ ፈረሴን
ራሴው ፈቅጄ ቃል ገብቻለሁ
እንኳን ያለኝን ራሴን እሰጣለሁ
ዳኛ ዳኛ የቀዬው ዳኛ
ከተረታሁ ይፍረድብኛ

እሷን ለኔ ብቻ ፈጥሯት
ከሩቅ ያየ መች አውቋት
ይሁን ማንም አይረዳት የልቤን ኩራት
አጋዥ አልፈልግም እኔ አለሁላት

ምግባሯን ሊዳኟት ቢሰጧት ጊዜ
ፍቅር የሚያዩባት ናት ድጋፍ ምርኩዜ
አምላኬን ከልቤ ከእውነት ካንጀት
ለእሷ አይደል ወይ ታዲያ አሜን ያልኩት
በእሷ ካፈርኩኝ ይፍረደኛ
ዳኛ ዳኛ የቀዬው ዳኛ (አቤት)
ከተረታሁ ይፈረድብኛ
አፍሬ በሷ ባጥፍ ምላሴን
ንብረቴን ልጣ ሰንጋ ፈረሴን
ራሴው ፈቅጄ ቃል ገብቻለሁ
እንኳን ያለኝን ራሴን እሰጣለሁ
ዳኛ ዳኛ የቀዬው ዳኛ
ከተረታሁ ይፈረድብኛ
ዳኛ ዳኛ የቀዬው ዳኛ
ከተረታሁ ይፈረድብኛ
ዳኛ ዳኛ የቀዬው ዳኛ
ከተረታሁ ይፈረድብኛ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists