Kishore Kumar Hits

Gossaye Tesfaye - Yale Fikir Kentu lyrics

Artist: Gossaye Tesfaye

album: Siyamish Yamegnal


ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር
ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር
ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር
በሀገር ተሞ ክብሬ ሁሉም ሰው ቢለኝ አንቱ
ያለ ፍቅር ከንቱ
አይደላኝ ኧረ እኔ ስሜ በመፍራቱ
መውደድ ነው ኩራቱ
ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር
ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር
ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር
ሳይጎላብኝ ስሜ ባልባል ጀግና ጌታ
ልኑር የትም ቦታ
አያርገኝ ኧረ እኔ ታላቁን እስክንድር
ባሻኝ እንዳድር
የዓለም የፍቅር ቀን ሲወሳ
ያቃል ባየው አበሳ
ለሱ ነው ልቤ የሚሳሳ
የሮማን ግንብ ያፈረሰው
ቢራራ ላፈቀረው ሰው
አጃቢው ቢሆንም ሚሊዮን
ሳይተካኝ በናፓሊዮን
አደራ ይስጠኝ ለ ፅዮን
አዛኟ እንደምትረዳኝ
ከሰው ጋር ታኑረኝ አዋዳ
አይፍራ
ወዶ የሚፀና
አይፍራ
ጠብቆ ቃልኪዳን
አይፍራ
ለሰው የሚኖር ሰው
አይፍራ
ቅርብ ነው ለመዳን
አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ
አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ
ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት
የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት
አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ
አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ
ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት
የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት
ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር
ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር
ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር
በሀገር ተሞ ክብሬ ሁሉም ሰው ቢለኝ አንቱ
ያለ ፍቅር ከንቱ
አይደላኝ ኧረ እኔ ስሜ በመፍራቱ
መውደድ ነው ኩራቱ
እርቄ ከፍቅር ጎዳና
አስቤ በገናገና
ተብዬ ለመኖር ጀግና
በፍርሃት ሰውን ለማራቅ
አይደንድን ልቤ እንደ ጎልያድ
እንደ ቂል ሲያሳየኝ ዘመንን
ታሪኳ ሲያመጣት በዓይኔ
ፍቅር ነች እራሷ ለኔ
ወጣቷ ያገሬ ንግስት
ሰው ነበር የልቧ ስስት
ተው ጌታ ... አፍስብኝ ለዛ
ተው ጌታ ... ከሰው እንዳልርቅ
ተው ጌታ ... አርገኝ እንደ ዳዊት
ተው ጌታ ... ቃሉ እንደሚያምርለት
አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ
አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ
ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት
የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት
አጉል ክብር አግኝቼ ፍቅር ከማጣ
ይበጀኛል እኔስ ከቤት ባልወጣ
ወትሮም ትልቅነት መምጫው መንገዱ
ሲሰጥ ነው ከላይ የሰው መውደዱ
አጉል ክብር አግኝቼ ፍቅር ከማጣ
ይበጀኛል እኔስ ከቤት ባልወጣ
ወትሮም ትልቅነት መምጫው መንገዱ
ሲሰጥ ነው ከላይ የሰው መውደዱአፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ
አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ
ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት
የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists