Gossaye Tesfaye - Hasab Yeleshim lyrics
Artist:
Gossaye Tesfaye
album: Siyamish Yamegnal
ምንድን ነው ቅሬታሽ ሚሰማሽ
ምን በድዬሽ በእኔ የተከፋሽ
ሳትነግሪኝ ሸኘኝ እንዳትይኝ
አንቺ ነሽ የውስጤ ብርታቱ
ብዬ እንዳልተናገርኩ ለስንቱ
አስገመትሽኝ በሰው እረ ተይ
ውስጤንም አመሳቅለሽ ሳታባሪ
ደጅ እምትናፍቂ ሰው ውሎ አዳሪ
ስትሆኚ ዝም አልኩ አንቺን ላለማጣት
ተይ ግን ጡር አይደለም ወይ ፍቅር መግፋት
አሄሄሄ
♪
እንኳንስ ገላሽን ለሌላ አንደበትሽ ቀርቦ አያወራ
ይህንን አውቃለው ብዬ እንጂ
ላይክፋኝ አምሮብሽ ስትሄጂ
ታዲያ ያስቆጠረሽ ወርቅ እንደ መዳብ
ግዜው ነው እንዴ ወይስ ክፉ ሐሳብ
ያኛውን የእምነቴን አጣሁት ከእኔጋ
ሰጥተሽኝ ብትሄጂ ነፍሰ የሌለው ስጋ
ምን ብዬ ላውጋ
ሐሳብ የለሽም ሐሳብ የለሽም ስለ እኔ
ውሉም አልገባሽ መቼም ጽድቅ እና ኩነኔ
ሐሳብ የለሽም ሐሳብ የለሽም ስለ እኔ
ውሉም አልገባሽ መቼም ጽድቅ እና ኩነኔ
♪
ምንድን ነው ቅሬታሽ ሚሰማሽ
ምን በድዬሽ በእኔ የተከፋሽ
ሳትነግሪኝ ሸኘኝ እንዳትይኝ
አንቺ ነሽ የውስጤ ብርታቱ
ብዬ እንዳልተናገርኩ ለስንቱ
አስገመትሽኝ በሰው ኧረ ተይ
ውስጤንም አመሳቅለሽ ሳታባሪ
ደጅ ምትናፍቂ ሰው ውሎ አዳሪ
ስትሆኚ ዝም አልኩ አንቺን ላለማጣት
ተይ ግን ጡር አይደለም ወይ ፍቅር መግፋት
አሄሄሄ
♪
የማምነው ከእውነታው ባይገጥምም
ለአጉል አሳልፌሽ አልሰጥም
ስታውቂው እንዳልሆንክ ሰበቡ
መሄድን ልብሽን ማሰቡ
ታዲያ ያስቆጠረሽ ወርቅ እንደ መዳብ
ግዜው ነው እንዴ ወይስ ክፉ ሐሳብ
ያኛውን የእምነቴን እጣሁት ከእኔጋ
ሰጥተሽኝ ብትሄጂ ነፍስ የሌለው ስጋ
ምን ብዬ ላውጋ
ሐሳብ የለሽም ሐሳብ የለሽም ስለ እኔ
ውሉም አልገባሽ መቸም ጽድቅ እና ኩነኔ
ሐሳብ የለሽም ሐሳብ የለሽም ስለ እኔ
ውሉም አልገባሽ መቸም ጽድቅ እና ኩነኔ
ሐሳብ የለሽም ሐሳብ የለሽም ስለ እኔ
ውሉም አልገባሽ መቸም ጽድቅ እና ኩነኔ
ሐሳብ የለሽም ሐሳብ የለሽም ስለ እኔ
ውሉም አልገባሽ መቸም ጽድቅ እና ኩነኔ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist