Kishore Kumar Hits

Gossaye Tesfaye - Yitayegnal lyrics

Artist: Gossaye Tesfaye

album: Siyamish Yamegnal


ያም ደርሶ ያም ደርሶ
ባይኔ ይሄዳል ዘመን ተሻግሮ
ያም ያም ያም ደርሶ
ትዝታሽ ዛሬ ላይ ነግሶ
ያም ያም መጥቶ
ከያለበት ወጥቶ
ምን ልበልሽ ምን ያልታየኝ አለ
አብረን ቆመን ካይን የተከለለ
እንኳን ምስልሽ ቀርቶ
በህሪሽ ድንቁ
ባህሪሽ እፁብ ድንቁ
በአካል ገዝፎ ይታየኛል ነግቶ
ይታየኛል ያ ያንቺ ዘመን
ይታየኛልየጊዜን ካብ ስፍራን ሁሉን ሽሮ
ሁለመናሽ ይታየኛል
ይታየኛል ስፍራው ሁሉ አበባ ሆኖ ልብስ
ይታየኛል የጨዋታሽ ሳቅ ድግስ
ይታየኛል አብረን ያደረግነው ደቂቅ ልሂቁ
ይታየኛል ይ ታ የ ኛ ል
ሌሊቱ ያንቺን መሰል ታትሞ
ሌሊቴን ካንቺው ዘመን ላይ ቆሞ
ከነበርንበት ከዛ የሳቅ ድግስ
ያሳድረኛል ምን አንቺን ባይመልስ
ምን ልበል እንዳታውቂው መች ኖሮ
ትዝታው ያሁን ያህል ተስሎ
ጉድ እስክንባል መቼም የትም ሆነን
የፍቅርን ዜማ ያዜምነው ተቃቅፈን
ፀሀይ ጨረቃ ምንም ናቸው
ምንም ናቸው
ካንቺ ጋር ቀረ ውበታቸው
ባንቺ ያልተገራ ምን ተገኛ
ምን ተገኘ
ፍቅርሽ ሲነካው ያልተቃኘ
ፀሀይ ጨረቃ ምንም ናቸው
ካንቺ ጋር ቀረ ውበታቸው
ባንቺ ያልተገራ ምን ተገኛ
ምን ተገኘ
ፍቅርሽ ሲነካው ያልተቃኘ
ይታየኛል ያ ውብ ዘመን ዛሬን መልሶ
በፍቅርሽ ልቤ ርሶ
ይ ታ የ ኛ ል
ካንቺ ጋር ቀረ
ፀሀይ ጨረቃ
ይታየኛል እኔኔ
ፀሀይ ጨረቃ
ካንቺ ጋር ቀረ
ፀሀይ ጨረቃ
ቀረ ቀረ
ፀሀይ ጨረቃ
ካንቺ ጋር ቀረ
ፀሀይ ጨረቃ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists