Kishore Kumar Hits

Gossaye Tesfaye - Alekaye lyrics

Artist: Gossaye Tesfaye

album: Single Collections


ገና ከጥንስሱ ፍቅር ያሳየችኝ ህይወቴ
ታዛዤ ነበረች ላባወራው አንደበቴ
አሁን መቼ ሰምታኝ ይመለስ ብል ጥያቄዬ
ፈላጭ ቆራጭ ሆና የቤቱ አዛዥ አለቃዬ
አለቃዬ
አለቃዬ የበላዬ
ስልጣንሽ በዝቶ ስቶኝ ከላዬ
ፍቅሩ እንዳይጠፋሽ ዋ ተይ
አንቺ አለቃዬ
አለቃዬ
አለቃዬ የበላዬ
እሷ ነበልባል ናት የእሳት ወላፈን
እልቅናዋ በዝቶ ወይኔ እንዴት ልፈናፈን
እራሴው ፈቅጄ ሰጥቻት ሹመት
በሱዋው ፍቃድ ሆነ
ወይ ጉድ ወጥቶም ለመግባት
ለምን ልነገታገት ለምን ልሟገት
አንዴ ካደረከኝ የእሳት እራት
ለማን አቤት ልበል የውስጤን ስቃይ
አንከራተተችኝ ሆና ከበላይ
አለቃዬ
አለቃዬ የበላዬ
ስልጣንሽ በዝቶ ስቶኝ ከላዬ
ፍቅሩ እንዳይጠፋሽ ዋ ተይ
አንቺ አለቃዬ
አለቃዬ
አለቃዬ የበላዬ
አልተዋት ነገር በሷ ጨክኜ
አመሏ ግራ መውደዷ ቀኝ
ቁጣዋ ሲበርድ ደሞ ሲላት
ነብሷን የምትሰጥ አፍቃሪ ናት
እኔው ብሾማት አለቃ አድርጌ
ክብሬ ተቆጣ ወይ ጉድ ዝና ማረጌ
ፈላጭ ቆራጭ ፍቅሯ ተቆጪ
ፍንክች የለም ካለችው ውጪ
እሺ ይሁን ይብዛ ስቃዬ
መኖር ካልቻልኩ ያለ አለቃዬ
አለቃዬ አንቺ አለቃዬ
አፍቃሪ እንጂ አትሁኝ ስቃዬ
ገና ከጥንስሱ ፍቅር ያሳየችኝ ህይወቴ
ታዛዤ ነበረች ላባወራው አንደበቴ
አሁን መቼ ሰምታኝ ይመለስ ብል ጥያቄዬ
ፈላጭ ቆራጭ ሆና የቤቱ አዛዥ አለቃዬ
አለቃዬ የበላዬ
ስልጣንሽ በዝቶ ስቶኝ ከላዬ
ፍቅሩ እንዳይጠፋሽ ዋ ተይ
አንቺ አለቃዬ
አለቃዬ የበላዬ
አዛዥ እና ታዛዥ ተቀያይሮ ዛሬ
ቅጥ አጣ ዘመኑ
ወይ ጉድ ቸገረ ለወሬ
ልተዛዛት እንጂ ካፌ ቃል ሳይወጣ
ተሸንፎ ማደር መቼስ ባገሩ ከመጣ
ኧረ እንዴት ይገፋል
አይጣል ነው ዘንድሮ
ከዚህ ካመሏ ጋር
እርሜ የእሳት ኑሮ
ለማን አቤት ልበል
የውስጤን ስቃይ
አንከራተተችኝ ሆና ከበላይ
አለቃዬ የበላዬ
አልተዋት ነገር በሷ ጨክኜ
አመሏ ግራ
መውደዷ ቀኝ
ቁጣዋ ሲበርድ ደሞ ሲላት
ነብሷን የምሰጥ አፍቃሪ ናት
ፍቅሯ እሳት ልቧ ገራገር
ወይ አይወጡት አይተፉት ነገር
ካልኖርኩላት ጠብ እርግፍ ብዬ
ቁጣ ብዙ ናት አለቃዬ
አለቃዬ አንቺ አለቃዬ
አለቃዬ አንቺ አለቃዬ
አለቃዬ አንቺ አለቃዬ
አፍቃሪዬ እንጂ አትሁኝ ስቃዬ
አለቃዬ የበላዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists