Kishore Kumar Hits

Gossaye Tesfaye - Adera lyrics

Artist: Gossaye Tesfaye

album: Single Collections


በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ
ባስበው ተጉዤ ወደኋላ
እኔስ አጣሁ መላ
ይቅርና ማሰብ በትካዜ
አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ
በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ
በሃሳብ አስታውሼ ወደኋላ
እንባ ባይኔ ሞላ
ይቅርና ማሰብ በትካዜ
አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ
ክፉ ደግ ላሳየኝ በህይወት ዘመኔ
ክብሩ ይመስገን ለአምላክ ልበል አስቀድሜ
በአራቱም ቅኝቶች ዜማን ተቀኝቼ
ቅርስ አስረክቤአለሁ ላሉት ወገኖቼ
አንቺ ሆዬ ባቲ አምባሰል ትዝታ
ከነፍስህ የወጣው የጥበብ ስጦታ
ያወረስከን ሙያ ሳይቀር ተደብቆ
ይኖራል ከኛ ጋር ክብርህን ጠብቆ
አደራ እላለሁ ደግሜ
ለጥበብ በቆየው ስሜ
አትዘን ሃሳብ አይግባህ
ያፈራል ዛሬም አበባህ
አይባባም አይባባም ሆዴ
አይባባም አይባባም ሆዴ
እስካለ መጪው ትውልዴ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ሙያዬን የሚቀበለኝ
በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ
ባስበው ተጉዤ ወደኋላ
እኔስ አጣሁ መላ
ይቅርና ማሰብ በትካዜ
አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ
በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ
በሃሳብ አስታውሼ ወደኋላ
እንባ ባይኔ ሞላ
ይቅርና ማሰብ በትካዜ
አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ
የዘመኔን ዋርካ ግንዱን ተጠግቼ
ይኸው አዜማለሁ ዕውቀቱን አግኝቼ
ከቀደሙኝ ማወቅ ሆኖልኝ መላዬ
ተምሬአለሁ ብዙ እኔም ከ ጥላዬ
ያሬዳዊ ዜማ በሚያንቆረቁረው
ተቀበልኩ አደራ በድምፅህ በሚያምረው
መቼም ላላጠፋው ጥበብን ከደሜ
ባገር ፊት ቃል ልግባ ከመድረኩ ቆሜ
አደራ እላለሁ ደግሜ
ለጥበብ በቆየው ስሜ
አትዘን ሃሳብ አይግባህ
ያፈራል ዛሬም አበባህ
አይባባም አይባባም ሆዴ
አይባባም አይባባም ሆዴ
እስካለ መጪው ትውልዴ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ሙያዬን የሚቀበለኝ
አይባባም አይባባም ሆዴ
እስካለ መጪው ትውልዴ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ሙያዬን የሚቀበለኝ
አይባባም አይባባም ሆዴ
አይባባም አይባባም ሆዴ
እስካለ መጪው ትውልዴ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ዛሬማ ተተኪም አለኝ
ሙያዬን የሚቀበለኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists