Gossaye Tesfaye - Satamehagn Bila lyrics
Artist:
Gossaye Tesfaye
album: Satamagne Bela
እንዴት ኧረ እንዴት እንዴት ይታሰባል
ሰው እንዴት እራበኝ ብሎ እምነቱን ይበላል
ግድ ነው የግድ ነው የኔስ መሰደዴ
ብርቅም ተከተለኝ የማያልቀው ጉዴ
ጉዴ አይ ጉዴ
ጉዴ አይ ጉዴ
አንቺም ትዳሬ ነሽ እሱም ጓደኛዬ
ጥፋቱ የማን ይሁን ታዲያ ስሄድ አንቺን ጥዬ
አወይ ክፉ ዘመን ልቤ አዘነብሽ
እሱም ተሳሳተ የኔ እናት አንቺም አልታመንሽ
ታማኝ ያንቺ ገላ ያለኔማ አያውቅም
ምነው ደከመሳ አነሰው ወይ አቅም
ስደተኛ ታርገኝ ደሞ ብላ ብላ
ጅብ እራብ አይችልም ወንድሜ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ፈራጅ አንተው ጌታ በፈጠርከው ገላ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ፈጣሪን አልፈራች ግፍ አይደርስም ብላ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ፈራጅ አንተው ጌታ በፈጠርከው ገላ
♪
እንዴት ኸረ እንዴት እንዴት ይታሰባል
ሰው እንዴት እራበኝ ብሎ እምነቱን ይበላል
ግድ ሆነ የግድ ነው የኔስ መሰደዴ
ብርቅም ተከተለኝ የማያልቀው ጉዴ
ጉዴ ዋይ ጉዴ
ጉዴ አይ ጉዴ
ባልጋ ባንድ ምሽት ናድክ የኔን ውለታ
ምን ታደርገኝ ነበር ወዳጄ ብትሆን በኔ ቦታ
ታማኝ ባል'ንጀራ ቢራብ ጾሙን ውሎ
ለእምነቱ ያድራል እንጂ ጥሩ ወዳጅ ለነገ አስተውሎ
ደረትህ ገላዋን ሲመኝ ለመኝታ
ዛሬን ልተፀፀት መች አሰብከው ላፍታ
አታብዛብኝ ምክንያት ከንግዲ አትደርድር መሀላ
ጅብ እራብ አይችልም ወንድሜ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
በስጋዊ ስሜት እየነደደ ገላህ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ፀፀትክ ምን ሊረባኝ ካረገው በዋላ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ሳታማሀኝ
ሳታማሀኝ ብላ ሳታማሀኝ ብላ
ፈራጅ አንተው ጌታ በፈጠርከው ገላ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist