Gossaye Tesfaye - Konjiye lyrics
Artist:
Gossaye Tesfaye
album: Satamagne Bela
ሸጋ ልጅ በሃሳቤ
ድንገት ልቤ ገብታ
ትመላለሳለች
ቀን ማታ ቀን ማታ
ቀን ማታ ቀን ማታ
ሃሳብ ገባው ልቤን
እረፍት የለው ፋታ
ዛሬ ነገ ሳትይ
ካለሽበት ቦታ
በአካል ድረሺልኝ
በትዝታሽ ፋንታ
በአካል ድረሺልኝ
በትዝታሽ ፋንታ
♪
እኔ እንዳለሁ አለሁ
ዛሬም በትዝታ
ዛሬም በትዝታ
አመል ልምድ ሆኖብኝ
ሄዳለሁ ቀን ማታ
ቀን ማታ ቀን ማታ
ሰው ፈልጎ አያጣኝ ወይኔ
ካገኘሁሽ ቦታ
ብትን ሃሳቤ ይሰበሰባል
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
አይኔም እንቅልፉን ያኔ ያሸልባል
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
አንዴ ብቅ በይ አደቤን ልግዛ
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
አያድርስ ነው ኧረ እዳው በዛ
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
ወደው የጓጉትን የሸጋ ልጅ ገላ
ቢመጠጥ አይጠግቡት እንደ ከረሜላ
የት ነሽ እንደሚለው የወደደሽ ቀልቤ
ጣፍጦ አለማለቅን አሳዪው ለልቤ
♪
ሸጋ ልጅ በሃሳቤ
ድንገት ልቤ ገብታ
ትመላለሳለች
ቀን ማታ ቀን ማታ
ቀን ማታ ቀን ማታ
ሃሳብ ገባው ልቤን
እረፍት የለው ፋታ
ዛሬ ነገ ሳትይ
ካለሽበት ቦታ
ደራርበሽ ነይልኝ
የፍቅርሽን ኩታ
ደራርበሽ ነይልኝ
የፍቅርሽን ኩታ
♪
ማነው ሰው ልመድ የሚለኝ
ደግሞ ካንቺ ሌላ
ለኔ ካንቺ ሌላ
ሲሆን አይደለም ወይ
እዬዬም ሲደላ
እዬዬም ሲደላ
ላንድ ራሴም አልሆንኩ ተይኝ
እንኳን ላስብ ሌላ
ተመስገን ማለት ለምዶበት አፌ
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
አለሁ እላለሁ ናፍቆት ታቅፌ
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
አታንሺው የኔን ሃሳብ ሰቀቀን
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
ብቻ ባየሽኝ መተሽ ለአንድ ቀን
እስኪ ነይ ቆንጅዬ
በሰላም አውለኝ የሚሉት ፀሎት
ስንቅ አልነበረም ወይ ወጥቶ ለመግባት
ምነው አሸከመኝ የቆንጆ ናፍቆት
ነፍሴን ለሱባዔ አብቃት እያልኩት
ወደው የጓጉትን የሸጋ ልጅ ገላ
ቢመጠጥ አይጠግቡት እንደ ከረሜላ
የት ነሽ እንደሚለው የወደደሽ ቀልቤ
ጣፍጦ አለማለቅን አሳዪው ለልቤ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist