Kishore Kumar Hits

Gossaye Tesfaye - Min Adergalehu lyrics

Artist: Gossaye Tesfaye

album: Satamagne Bela


በፍቅር ስንኖር ለአመታት ምንም ያልመሰላቸው
እናቴስ ብለው ጠየቁኝ ልጆችሽ ብትርቂያቸው
አንቺን በማጣት ሲራቡ በናፍቆት አትቅጫቸው
የኛ አንዴ ሆኗል ግድየለም ዛሬን መተሽ እያቸው

የህይወት አጋር የለኝ ጠፍቶኝ የማማክረው
ሰው እንዳይኖር ከልቤ ቃል ኪዳኔን አልሰብረው
ሲጠይቁኝ ቢጨንቀኝ ተፈቶ አንደበታቸው
እስከመቼ ሰው ሀገር ናት ብዬ ልዋሻቸው
ምን አደርጋለሁ እኔ
ብቻዬን ሆኜ ዛሬ
ቢጠፋ ሰው ፊት ቀልቤ
ለነሱ አዝኖ እንጂ ልቤ

ተዋደን ስንኖር ላመታት ምንም ያልመሰላቸው
እናቴስ ብለው ጠየቁኝ ልጆችሽ ብትርቂያቸው
አንቺን በማጣት ሲራቡ በናፍቆት አትቅጫቸው
የኛ አንዴ ሆኗል ግድየለም ዛሬ መተሽ እያቸው

አይሆንም ያሉት ነገር በሱ ፍቃድ ይሆናል
ምንስ ሌላ ብትወጂ መች በልጅ ይጨከናል
ግዴለም ቢሉኝ እኔን ምነው ዛሬስ ያለሷ
ቀርቶብኝ አለው አይራቃቸው መንፈሷ
ምን አደርጋለሁ እኔ
ብቻዬን ሆኜ ዛሬ
ቢጠፋ ሰው ፊት ቀልቤ
ለነሱ አዝኖ እንጂ ልቤ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists