Kishore Kumar Hits

Haileye Taddesse - Me'techalehu lyrics

Artist: Haileye Taddesse

album: Hulie Hulie ( Ethiopian Contemporary Music)


መጥቻለሁ ልብሽ ከፈቀደ
ይኸው እምባዬም ስላንቺ ወረደ
ሲርቅብኝ ድምፅሽ ከጆሮዬ
እኔው መጣሁ ያለቀጠሮዬ
የሰማይ...
ውብ ጨረቃ በኮኮብ ተከባ
አይቻለሁ መሬት ስትገባ
አንቺም የለሽ ምሽቱም ጠቆረ
ውበትሽም አብሮ ተቀበረ
ልቤም አዝኖ ካንቺውጋ ነጎደ
ከማረፊያው አብሮ ተሰደደ
ልቤም አዝኖ ካንቺውጋ ነጎደ
ከማረፊያው አብሮ ተሰደደ
ሀሳብ ዞሮ ባረፍሽበት ይረፍ
ከማጠኛው ከመቅደሱ መንገድ
መጥቻለሁ ልብሽ ከፈቀደ
ይኸው እምባዬም ስላንቺ ወረደ
ሲርቅብኝ ድምፅሽ ከጆሮዬ
እኔው መጣሁ ያለቀጠሮዬ
የኔማ...
ዕምባ ቤቴ ገባና ከረመ
ልቤም በሀሳብ በሀዘንሽ ታመመ
ደጀሰላም የዘላለም ቤትሽ
እየዋለ ይደር ሲጠብቅሽ
ልቤም አዝኖ ካንቺውጋ ነጎደ
ከማረፊያው አብሮ ተሰደደ
ልቤም አዝኖ ካንቺውጋ ነጎደ
ከማረፊያው አብሮ ተሰደደ
ሀሳብ ዞሮ ባረፍሽበት ይረፍ
ከማጠኛው ከመቅደሱ መንገድ
ልቤም አዝኖ ካንቺውጋ ነጎደ
ከማረፊያው አብሮ ተሰደደ
ሀሳብ ዞሮ ባረፍሽበት ይረፍ
ከማጠኛው ከመቅደሱ መንገድ
ልቤም አዝኖ ካንቺውጋ ነጎደ
ከማረፊያው አብሮ ተሰደደ
ሀሳብ ዞሮ ባረፍሽበት ይረፍ
ከማጠኛው ከመቅደሱ መንገድ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists