Kishore Kumar Hits

Haileye Taddesse - Sinor lyrics

Artist: Haileye Taddesse

album: Hulie Hulie ( Ethiopian Contemporary Music)


ሲኖር መተባበሩ
ሲኖር መፈቃቀሩ
ሲኖር ህይወት ይደምቃል
ሲኖር ውጥን ይሰምራል
አንደኛው ለአንደኛው ሲኖር ነው
ሲኖር ነው ፍቅር የሚባለው
ሲኖር መተባበሩ
ሲኖር መፈቃቀሩ
ሲኖር ህይወት ይደምቃል
ሲኖር ውጥን ይሰምራል
አንደኛው ለአንደኛው ሲኖር ነው
ሲኖር ነው ፍቅር የሚባለው
እውነተኛን ስሜት በልብ አመንጭቶ
ሁሉም ካልረካበት እኩል ተጎንጭቶ
ከቀረበው ቆርሶ ካልተጎራረሰ
ፍቅር ይሄን አቶ ምኑ ዳር ደረሰ
አንቺ ትብሽ አንተ እየተባባለ
አንደኛው ለአንደኛው እራብን ካልዋለ
ራስን አስበልጦ ለራስ ብሎ ማደር
ፍቅር ሊባል ነው ወይ እስኪ እንነጋገር
ሁሌም እጅ ለእጅ ከተያያዙ
ሰው መሆን አይቀር ልብ እየገዙ
ግን ከራስ በላይ ንፋስ ነው ካሉ
የፍቅርን ውጥንን መች ያሳካሉ
ሁሌም እጅ ለእጅ ከተያያዙ
ሰው መሆን አይቀር ልብ እየገዙ
ግን ከራስ በላይ ንፋስ ነው ካሉ
የፍቅርን ውጥንን መች ያሳካሉ
ላይ ላይ ላይ
ሲኖር መተባበሩ
ሲኖር መፈቃቀሩ
ሲኖር ህይወት ይደምቃል
ሲኖር ውጥን ይሰምራል
አንደኛው ለአንደኛው ሲኖር ነው
ሲኖር ነው ፍቅር የሚባለው
ሲኖር መተባበሩ
ሲኖር መፈቃቀሩ
ሲኖር ህይወት ይደምቃል
ሲኖር ውጥን ይሰምራል
አንደኛው ለአንደኛው ሲኖር ነው
ሲኖር ነው ፍቅር የሚባለው
እዳውን ሲመልስ እየተጋገዘ
ልቡን አንድ አድርጎ ኑሮውን ከያዘ
ችግርና ደስታን ካለፈው ተጋራ
ይህ ነው የሚያዘልቀው ሰውን ከሰው ጋራ
በመዋደድ አለም ካንጀት ተወዳጅቶ
ህይወትን ሲያምርባት ፍቅሩን አቆንጅቶ
ውጥኑን አሳክቶ ከዳሩ ሲያደርሰው
ተደጋግፎ ሲኖር ያምራል ሰውና ሰው
ሁሌም እጅ ለእጅ ከተያያዙ
ሰው መሆን አይቀር ልብ እየገዙ
ግን ከራስ በላይ ንፋስ ነው ካሉ
የፍቅርን ውጥንን መች ያሳካሉ
ሁሌም እጅ ለእጅ ከተያያዙ
ሰው መሆን አይቀር ልብ እየገዙ
ግን ከራስ በላይ ንፋስ ነው ካሉ
የፍቅርን ውጥንን መች ያሳካሉ
ላይ ላይ ላይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists