Kishore Kumar Hits

Mulatu Astatke - Tsome Diguwa lyrics

Artist: Mulatu Astatke

album: Ethio Jazz Vol. 1


እ' ምነው ወዳጄ ምነው
እዚያ ላይ ያለች ሸክላ ሰሪ
ድሃ ናት አሉኝ ፆም አዳሪ
ማን በነገራት ጥበቡን
ገል አፈር መሆኑን
•••
እ' ምነው ወዳጄ ምነው
ትንሽ ቤት ሰራኹኝ ዳግመኛ
ሁለት ሶስት ሰው የሚያስተኛ
አላስገባ አለች እሷው ጠባ
ሰው በሰው ላይ እየገባ
•••
እ' ምነው ወዳጄ ምነው
ከወጥ ቤት ሄጄ ድንገት
ቋንጣ ጠብሼ ለመብላት
ወድቄ ነበር ከ'ሳት ላይ
ስጋ ስጋዬን ሳይ
•••
እ' ምነው ወዳጄ ምነው
የልጃገረድ አውታታ
ካ'ውራ መንገድ ላይ ተኝታ
ተነሽ በሏት ምነው
ይህ ሁሉ አለም አፈር ነው
•••

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists