Kishore Kumar Hits

Esubalew Yetayew - Hiyaw Seim lyrics

Artist: Esubalew Yetayew

album: Tertaye


አካል ኖሮት እንደሰው
ህያው ሆናል ስራቸው
አካል ኖሮት እንደሰው
ህያው ሆናል ስራቸው
አካል ኖሮት እንደሰው
ህያው ሆናል ስማቸው
ኧረ ደኑ ዎ
ኧረ ደኑ
ላንሳ ያንን ጀግና ሰው
ኧረ ደኑ ዎ
ኧረ ጫካው
ላንሳት ያቺን ጀግና ሰው
ስንት ጀግኖች ወድቀው በሀገራችን ምድር
ላቆዩልን ዛሬ ይህቺን መሰል ሀገር
ከጊዜያቸው ቀድመው ነገን እያለሙ
ክብር ይሁን ሁሌም ሀገር ላስቀደሙ
ምንም በሌለበት ቀድመው የጀገኑ
በጀብድ ታሪካቸው በጣም የገነኑ
ከእምዬ ኢትዮጵያ ከታሪክ ማህደር
መች ተነግሮ ያልቃል የጀግኖቿ ነገር
ጎራው ና ጎራው ና
ጎራው ና ጎራው ና ጎራው ና ጎራው ና
ጎራው ና ጎራው ና ጎራው ና ጎራው ና
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
መች ይቀመጣል ዘራፍ ሲነሳ
ልቡ ድፍን ነው ልክ እንደ አንበሳ
አቧራው ጨሶ ደም ደም ሲመስል
አባሮ ገዳይ ከዳመናው ስር
እኔ የዛ ሰው ነኝ የሐበሻ ምድር
ወኔን አስታጣቂ ከሞት የሚምር
ከአንድ ወንዝ የምቀዳ
የእሳት ልጅ ነኝ እሳት
የምኖር በክብር
የምኖር በኩራት
ለሀገር መሞት ክብርን ያን ወኔውን ወሳጅ
እኔ የዛ ሰው ነኝ የጥቁር ደም ውላጅ
አደራ ጠባቂ የአካሉ ግማጅ
ለሀገራቸው ታመው ላገር ስለሞቱት
ህይወት እድሜያቸውን አካል ለገበሩት
ለህልውናዋ ዘብ ሆነው ላለፉት
ልንዘምር ይገባል ሀገርን ላቆዩት
የተከሉት ውብ ስም ዘመን የማይንደው
መቃብርን ፈንቃይ ሞት የማይጋርደው
ለዛሬ በማሰብ ትናንትን የደሙ
በሞታቸው ሰላም ነጻነት ሸለሙ
አካል ኖሮት እንደሰው
ህያው ሆናል ስራቸው
ያቺ የሀገሬ ጀግና
አካል ኖሮት እንደሰው
ህያው ሆናል ስማቸው
ያቺ የሀገሬ ጀግና
አካል ኖሮት እንደሰው
ህያው ሆናል ስማቸው
አካል ኖሮት እንደሰው
ህያው ሆናል ስራቸው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists