Esubalew Yetayew - Degmo Demo lyrics
Artist:
Esubalew Yetayew
album: Tertaye
ስላንቺ ሰው ቢነግረኝም
ልለይሽ ፍፁም አልቻልኩም
እንዳልቆርጥ አቃተኝ እንዳልቆርጥ
ከሰው አላየሁሽ እንዳልቆርጥ
ደግሞ ደግሞ ይታየኛል ውበትሽ
ሳስብ ልለይሽ
ደግሞ ደግሞ ይመጣናን ያ ፈገግታሽ
ድቅን ይላል ሳቅሽ
ትሄጃለሽ ይሉኛል ወዳጅ አፍርተሽ ሌላ
ቤት ምሰሷችን ሳይፈርስ ማተባችን ሳይላላ
እንደምን ብየ ልመን ምንስ ሰበብ አግኝቼ
አላጎደልሽብኝም እንዴት ልጥላሽ ሰምቼ
እንዳልቆርጥ አቃተኝ እንዳልቆርጥ
ከሰው አላየሁሽ እንዳልቆርጥ
ደግሞ ደግሞ ይታየኛል ውበትሽ
ሳስብ ልለይሽ
ደግሞ ደግሞ ይመጣናን ያ ፈገግታሽ
ድቅን ይላል ሳቅሽ
ድቅን ይላል ሳቅሽ
ውበቱ አስኪ ምንድን ነው ቤቴ ያላንቺ ፍቅር
ሆኖለትስ እረስቶሽ ልቤ ይችላል ወይ መኖር
ብሮጥ እንኳን አላመልጥ አንደንስር በርሬ
ሁሉ ቦታዬ አንቺው ነሽ ሁነሻል ሰማይ ምድሬ
እንዳልቆርጥ አቃተኝ እንዳልቆርጥ
ከሰው አላየሁሽ እንዳልቆርጥ
ደግሞ ደግሞ ይታየኛል ውበትሽ
ሳስብ ልለይሽ
ደግሞ ደግሞ ይመጣናን ያ ፈገግታሽ
ድቅን ይላል ሳቅሽ
ድቅን ይላል ሳቅሽ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist