Kishore Kumar Hits

Esubalew Yetayew - Ende Weyin lyrics

Artist: Esubalew Yetayew

album: Tertaye


እንደ አዲስ ሲቆይ ጣዕሙ ከርሞ የሚጨምር
እንደ ወይን ሆነብኝ ዘወትር ልዩ ያንቺስ ፍቅር
እንደ ወይን ተወዳጅ ነሽ በቀን በቀን
እንደ ወይን ጣዕምሽ ልዩ በቀን በቀን
እንደ አዲስ ሲቆይ ጣዕሙ ከርሞ የሚጨምር
እንደ ወይን ሆነብኝ ዘወትር ልዩ ያንቺስ ፍቅር
እንደ ወይን ተወዳጅ ነሽ በቀን በቀን
እንደ ወይን ጣዕምሽ ልዩ በቀን በቀን
የጥፍጥናው ሚስጥሩ መቆየቱ ጊዜው በሄደ ቁጥር መፈለጉ
አመታትን ሲጨምር ነው ጣዕሙ ቀን በቀን መወደዱ የወይን ወጉ
እለት በለት አዲስ ጊዜው ሲርቅ ሲሄድ
እንደ ወይን ሆነብኝ የኔና ያንቺ መዉደድ
ተመኘሁ በግድ እስክንቀር ሳፈቅርሽ ልኖር አብሬ
አድሜየ ማምሻ ድረስ ጉም እስኪመስል ፀጉሬ
እንደ ወይን ተወዳጅ ነሽ በቀን በቀን
እንደ ወይን ጣዕምሽ ልዩ በቀን በቀን
አንቺ ወይኔ ይሄ ልቤ ማድጋሽ
ፍቅርን ማስቀመጫሽ ማደሪያሽ
ጣዕም አልባ ወና ውስጠቴን ደርሰሽ
በደስታ በሃሴት የሞላሽ
ቀን በቀን አዲስ ሰው በጉጉት ማገኝሽ
ሁሌ ተናፋቂ ሁልጊዜ ልዩ ነሽ
ተመኘሁ በግድ እስክንቀር ሳፈቅርሽ ልኖር አብሬ
አድሜየ ማምሻ ድረስ ጉም እስኪመስል ፀጉሬ
እንደ ወይን ተወዳጅ ነሽ በቀን በቀን
እንደ ወይን ጣዕምሽ ልዩ በቀን በቀን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists