ለካ የሞተው የበሬው አንጀት ነው
ለካ ክራር ሆኖ ቤቴን የሞላው
ለካ የሸንበቆው ስባሪ ነው
አይ ለካ ዋሽንት ሆኖ ልቤን 'ሚያምሰው
ለካ ትዝታ ናፍቆትሽ ተዳምሮ
ለካ አቅሜን ያሳጣኝ ሰባብሮ
የሞተን በሬ ቆዳ ወጥረው
ቢደበደቡት ከበሮ ብለው
ምቱ አይመስጥም ህመም ብቻ ነው
ወዶ ላጣ ሰው ከበሬው ጋራ ትዝታ ላለው
አንጀቱ ደርቆ ክር ነው ብለው
እየወጠሩ አውታሩን ደርሰው
ግጥም ቢያወርዱ አይጥምም ዜማው
ወዶ ላጣ ሰው በሬውን ለሚያውቅ ትዝታ ላለው
ተዉ ተዉ ይሄን ከበሮ ተዉ
ተዉ ተዉ ይሄን ክራር ተዉ
አንቺ እኔን ለማየት የመጣሽበት ያ ሰጋር ፈረስ
እርጅና ይዞት ጉልበቱ ቢፈስ
ከሞተ ወዲያ ጭራውን ቆርጠው
ቢገዘግዙት መሰንቆ ብለው
ጣዕም አይሰጥም ህመም ብቻ ነው
ወዶ ላጣ ሰው ከፈረሱ ጋራ ትዝታ ላለው
ፍቅርን ስናወጋ በሻሻታው ድምፅ ዘመን በሚለው
ያን ሸንበቆውን ያን የምንወደው
አድርቀው ሰብረው ጎኑን በሳስተው
ዋሽንት ቢሉኝ ትንፋሽ ጨምረው
ለኔ ሚሰማኝ ህመም ብቻ ነው
አንቺን ነው እንጂ የሚያስታውሰኝ ሌላ ምን አለው
ተዉ ተዉ ይሄን መሰንቆ ተዉ
ተዉ ተዉ ይሄን ዋሽንት ተዉ
ትዝታ ሆኖ ሁሉ ኮሽታው
ናፍቆት ቤቱ አይኑ ማረፊያው
ዝም እንዲሉለት አቅሙ ተዉ ነው
የወደደውን ጊዜ ያሳጣውን
ትዝታ ሆኖ ሁሉ ኮሽታው
ናፍቆት ቤቱ አይኑ ማረፊያው
ዝም እንዲሉለት አቅሙ ተዉ ነው
የወደደውን ጊዜ ያሳጣውን
ተዉ ተዉ ይሄን ከበሮ
ተዉ ተዉ ተዉ ይሄን ክራር ተዉ
ተዉ ተዉ ይሄን መሰንቆ ተዉ
ተዉ ተዉ ይሄን ዋሽንት ተዉ
ተዉ ተዉ ዝም በሉ ተዉ
ተዉ ተዉ ተዉ ተዉ ተዉ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist