Kishore Kumar Hits

Esubalew Yetayew - Atgudel Kisey lyrics

Artist: Esubalew Yetayew

album: Tertaye


አልሂድ ከሰው ቤት አልመፅወተው
ላቤም አትድረቅ ይድላኝ ስኖረው
ከሰው አልጠብቅ ልትረፍ አልፌ ከራሴ
ሁልጊዜ ሙላ አትጉደል ኪሴ
ሁልጊዜ ሙላ አትጉደል ኪሴ
የሰው ፊት ካራው ስለቱ ፤ አይቁረጠኝ ከቶ አይውጋኝ
ጉልበቴ አትዛል አደራ ፤ ችግር አደራ አይየኝ
የማገኛት የላበቴ ፤ የወዜ ዋጋ ተባርካ
ትንሿ በዝታ ታርሰኝ ፤ በሀሴት በደስታ ልርካ
እ ... ለምን የሰው እጅ ኣየ ፤ እ ... እሻለው ደሞ
እ ... ካልተንተራሰ ኣየ ፤ እ ... ክንዴ ተዳክሞ
እ ... ያድለኝ እንጂ ኣየ ፤ እ ... ጤናውን ይስጠኝ
እ ... በላቤ አግኝቼ ኣየ ፤ እ ... ሰጪ መፅዋች ያርገኝ (አትጉደል ኪሴ)
በል አትጉደልብኝ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
ትዝብት አታሁነኝ ልዘዝህ እራሴ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
በል አትጉደልብኝ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
ከሰው አላበልጥህ ሎሌ ነህ የራሴ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
ለሆዴ ማደር አይደለም ፤ የሃሳቤ ዳር ምኞቴ
ፍቅሬን ካገኝሁ ትዝ አይለኝ ፤ ባዶ ቢሆንም ሌማቴ
አንዱ ቤት ብራ እየሆነ ፤ አንዱ ቤት ጨለማ ሰፍኖ
አንዱ ቤት አንዱን አይሰማ ፤ እንጀራ ውሃ ብር ሆኖ
እ ... ልብሰል ብየ እንጂ ኣየ ፤ እ ... ጊዜውን ልሁን
እ ... አውቃለሁ ፍቅሬን ኣየ ፤ እ ... ኪስ አይገዛውም
ግን ሰብሬ አንገቴን ኣየ ፤ እ ... ካላየ ሌላ
እ ... አትጉደል ኪሴ ኣየ ፤ እ ... ሁልጊዜ ሙላ (አትጉደል ኪሴ)
በል አትጉደልብኝ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
በል ከእንግዲህ ወዲህ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
ትዝብት አታሁነኝ ልዘዝህ እራሴ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
ከሰው አላበልጥህ ሎሌ ነህ የራሴ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)
አትጉደል ኪሴ
(በል አትጉደል ኪሴ አሃሃ በል አትጉደል ኪሴ አትጉደል ኪሴ)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists