Kishore Kumar Hits

Tibebu Workyie - Ebakshin Asbibet lyrics

Artist: Tibebu Workyie

album: Alamarrm (Ethiopian Contemporary Music)


ተለያዩ ሲባል ኧረ ሰዉ ምን ይለናል
እሺ የኛስ ይሁን የሰማ ሰው ምን ይለናል
ግዴለም አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል
እባክሽ አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል
ተለያዩ ሲባል ኧረ ሰዉ ምን ይለናል
እሺ የኛስ ይሁን የሰማ ሰው ምን ይለናል
ግዴለም አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል
እባክሽ አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል
ያየን እስኪደነቅ ማመን እስኪያቅተው
እንዲህም አይነት ፍቅር አለ ወይ እስኪል ሰው
ሳይቸግረን ያኔ ከዓይን ውስጥ ገብተናል
ጥላው ሄደች ቢባል አሁን ሰው ምን ይላል
እመነኝ ስትዪኝ ጎዳናው ሰምቶሻል
እንደኔ በደስታ ሳር ቅጠሉ አይቶሻል
ተለያዩ ሲባል መርዶውን አይወዱም
ቅጠሉም ይረግፋል ተይ ያዝናሉ እንደጉም
ፍቅራችንን ተመልክቶ ካይን ያውጣችሁ ያኔ ያለን
የሰማ ቀን ይተክዛል ድንገት ወረት ሲለያየን
የለመደሽ መስኪን ቤቴ ተይ ጭር ይላል ከሄድሽበት
እኔም ውስጤ ይሰበራል እባክሽን አስቢበት
ተለያዩ ሲባል ኧረ ሰዉ ምን ይለናል
እሺ የኛስ ይሁን የሰማ ሰው ምን ይለናል
ግዴለም አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል
እባክሽ አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል
በፍቅር የሚያውቀን ሲያጣሽ ፊቱ ጠቁሮ
እንደድሮው መስሎት ምነው ያለ ወትሮ
ብቻህን የት ሄደች ቢለኝ ሲያይ ከስዬ
መመለስ አልችልም ጥላኝ ሄደች ብዬ
በትንሽ ትንሹ አድርገው ከወሰዱት
አይገድልም ይባላል መርዝም ከለመዱት
ባይሆን ቀስ በቀስ ውስጤን እንዳይከብደው
ባክሽ ትንሽ ቆዪ ስቃዩን ብለምደው
ፍቅራችንን ተመልክቶ ካይን ያውጣችሁ ያኔ ያለን
የሰማ ቀን ይተክዛል ድንገት ወረት ሲለያየን
የለመደሽ መስኪን ቤቴ ተይ ጭር ይላል ከሄድሽበት
እኔም ውስጤ ይሰበራል እባክሽን አስቢበት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists