Kishore Kumar Hits

Bisrat Surafel - Zim Yalewin Firaw lyrics

Artist: Bisrat Surafel

album: Kal Bekal


ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ
ይጮሀል ለካ ዝምታ
ትግስቱ የበዛ
አይደለም የዋዛ
ይልቅ ከሚያወራው
ዝም ያለውን ፍራው
ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ
ይጮሀል ለካ ዝምታ
ትግስቱ የበዛ
አይደለም የዋዛ
ይልቅ ከሚያወራው
ዝም ያለውን ፍራው
እናት ዥንጉርጉር እውነትም ነው ሆዷ
አየሁ ሁለት ሰው ክፉ ደግ ወልዳ
አቤል ተከሶ ሰው ተኳርፎ ከይሉኝታ
ቃየል ነገሠ በምድሪቷ
በልጦበት ጥቅም ለዲናር ቆሞ
ወዳጅ ወዳጁን ይሸጣል ስሞ
አውቆ ነው ያ ሰው አንገት መድፋቱ
ዝም ያለው ጠልቶ እሪ በከንቱ
በልጦበት ጥቅም ለዲናር ቆሞ
ወዳጅ ወዳጁን ይሸጣል ስሞ
አውቆ ነው ያ ሰው አንገት መድፋቱ
ዝም ያለው ጠልቶ እሪ በከንቱ
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ
ይጮሀል ለካ ዝምታ
ትግስቱ የበዛ
አይደለም የዋዛ
ይልቅ ከሚያወራው
ዝም ያለውን ፍራው
ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ
ይጮሀል ለካ ዝምታ
ትግስቱ የበዛ
አይደለም የዋዛ
ይልቅ ከሚያወራው
ዝም ያለውን ፍራው
ቃል እየበላ ለማደር የዛሬን ጎርሶ
አለ የሚኖር ከአራዊት አንሶ
ይከበር እንጂ ጨዋ ሆኖ ድል አድራጊ
እውነት ተናግሮ ባመሸው አንጊ
ብልህ አይጥልም ቀድሞ በወሬ
ፍራ ዝምታን ልብ በል ዛሬ
አክብረው ስማ ያን ሰው ይልቅ
ስለመረጠ ዝምታን ወርቅ
ብልህ አይጥልም ቀድሞ በወሬ
ፍራ ዝምታን ልብ በል ዛሬ
አክብረው ስማ ያን ሰው ይልቅ
ስለመረጠ ዝምታን ወርቅ
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists