Bisrat Surafel - Zarem Kehuala lyrics
Artist:
Bisrat Surafel
album: Kal Bekal
ዛሬም ከኋላ ነገም ከኋላ
ታዲያ እስከመቼ ሆኜ እንደጥላ
ልሂድ ልከተል የራሴን እውነት
ሰው ሆኖ አይቻል ሁሉን ማስደሰት
ዛሬም ከኋላ ነገም ከኋላ
ታዲያ እስከመቼ ሆኜ እንደጥላ
ልሂድ ልከተል የራሴን እውነት
ሰው ሆኖ አይቻል ሁሉን ማስደሰት
ስጥር ከርሜ ስል ደፋ ቀና
ብደክም የልቤን ማን አየውና
ለሌላው ደስታ በቸረች ነፎሴ
እንዴት ልጎዳ እኔስ ለራሴ
ጎልቶ ከታየ ደካማ ጎኔ
አንተም እንዳይንህ አኔም እንዳይኔ
አትስጡኝ ምርጫ እኔ አለኝ መንገድ
አንዱን አልጠላም አንዱን ለመውደድ
ያለኔ መስመር አትሂድ ላለ
እየወደዱም መለየት አለ
አትስጡኝ ምርጫ እኔ አለኝ መንገድ
አንዱን አልጠላም አንዱን ለመውደድ
ያለኔ መስመር አትሂድ ላለ
እየወደዱም መለየት አለ
ዛሬም ከኋላ ነገም ከኋላ
ታዲያ እስከመቼ ሆኜ እንደጥላ
ልሂድ ልከተል የራሴን እውነት
ሰው ሆኖ አይቻል ሁሉን ማስደሰት
ለዚኛው ሀዘን ለዛኛው ደስታ
ሆኖ ባይሞላም የኔ ስጦታ
ከንፉግ ሲያየኝ ያጎደልኩበት
ስንቴ ተሰማኝ ጥፋተኝነት
አትንሳኝ አልኩተ እድሜና ጤና
ሲክስ ለሁሉም ግዜ አለውና
አትስጡኝ ምርጫ እኔ አለኝ መንገድ
አንዱን አልጠላም አንዱን ለመውደድ
ያለኔ መስመር አትሂድ ላለ
እየወደዱም መለየት አለ
አትስጡኝ ምርጫ እኔ አለኝ መንገድ
አንዱን አልጠላም አንዱን ለመውደድ
ያለኔ መስመር አትሂድ ላለ
እየወደዱም ሰው መራቅ አለ
የኔን ያዝ አትበለኝ
እኔም መንገድ አለኝ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist