Kishore Kumar Hits

Helen Berhe - Yehelme Gudegna [Remastered] lyrics

Artist: Helen Berhe

album: Tasfelgegnaleh [Remastered]


አላልኩም ህልም የለም ጠዋት ተነስቼ
ሳልተኛ አላደርኩም ህልሜንም ፈርቼ
በፊት ቶሎ ቶሎ ትመጣ ነበረ
ሰሞኑን ጠፍተሃል ብቻዬን ሳድር
የህልሜ ጓደኛ
ትመጣለህ ዛሬ በጊዜ ልተኛ
የህልሜ ጓደኛ
ልተኛ ደግሜ
መጽናኛ ነው ህልሜ
የህልሜ ጓደኛ
በል ቁርጡን ንገረኛ
በሰበብ ባስባቡ ደከመኝ እያልኩኝ
በጊዜ መተኛት እኔ እንደው አልተውኩኝ
ቀን አላስቸግርህ ለምጄዋለሁ
አትቅርብኝ በልሜ እጠብቅሃለሁ
ሳላይህ ከነጋ
ሌቱ ከቀኑ ጋ
ምን ለየሁ ብለህ ነው
በህልሜ አንተን ካላየው
ካላየሁ በል ናልኛ
ካላየሁ ብቸና ነኝና
ካላየሁ ያንተ እስረኛ
ካላየሁ ኤ ኤ ኤ ኤ

በስሜት ተግባብተው ምንም ሳይሰስቱ
ካፈቀሩት ጋራ በእውን ሲደሰቱ
እኔ ግን በምኞት ብቻዬን እያለሁ
ዛሬም በህልም አለም ከአንተ ጋር አድራለሁ
የህልሜ ጓደኛ
ትመጣለህ ዛሬ በጊዜ ልተኛ
የህልሜ ጓደኛ
ልተኛ ደግሜ
መጽናኛ ነው ህልሜ
የህልሜ ጓደኛ
በል ቁርጡን ንገረኛ
በሰበብ ባስባቡ ደከመኝ እያልኩኝ
በጊዜ መተኛት እኔ እንደው አልተውኩኝ
ቀን አላስቸግርህ ለምጄዋለሁ
አትቅርብኝ በልሜ እጠብቅሃለሁ
ሳላይህ ከነጋ
ሌቱ ከቀኑ ጋ
ምን ለየሁ ብለህ ነው
በህልሜ አንተን ካላየሁ
ካላየሁ በል ናልኛ
ካላየሁ ብቸና ነኝና
ካላየሁ ያንተ እስረኛ
ካላየሁ ኤ ኤ ኤ ኤ
ካላየሁ ኦ ኦ ኦ ኦኦ
ካላየሁ በል ናልኛ
ካላየሁ ብቸና ነኝና
ካላየሁ ያንተ እስረኛ
ካላየሁ ኤ ኤ ኤ ኤ
ካላየሁ ኦ ኦ ኦ ኦኦ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists