Kishore Kumar Hits

Helen Berhe - Kaduganaw [Remastered] lyrics

Artist: Helen Berhe

album: Tasfelgegnaleh [Remastered]


ሩቅ ሆኜ ሳለው
ጎኔ ያለህ ይመስለኛል
እንዴት እንደምወድህ
እንዴት እንደማፈቅርህ
ማን ይረዳልኛል ያቅልኛል
ስታስበው ደሞ
የሸሸሁ ከአንተ ውዴ
እድገት ቀንቶኝ ብመጣ
አምላክ ፈቅዶ ብመጣ
አትሸሸኝም እንዴ ባክህ ውዴ

ፍቅራችንን ሳስታውስ ሳወራው ሰው መሀል
ታድያ ለምን እራቅሽው ጨካኝ ነሽ ይሉኛል
ላልቀመሰው ላላየው ማጣት ከሩቅ ቀላል
እጅ ማየት ታውቃለህ የሰው ፊት ያስጠላል
ከአዱኛው ፈጣሪ ባይነሳኝ ሻልም ቢል ከበፊት ኑሮዬ
የልቤን የውስጤን አግኝቼ ቢሞላ ቢተርፍም ጓዳዬ
ላየኝ ሰው የጠላሁ ብመስልም አንተው ነህ በሀሳቤ ለኔ ግን
ከፀፀት አውጣኝ በይቅርታ ክሳለው ማረኝ የኔ ጌታ
ከአዱኛው ፈጣሪ ባይነሳኝ ሻልም ቢል ከበፊት ኑሮዬ
የልቤን የውስጤን አግኝቼ ቢሞላ ቢተርፍም ጓዳዬ
ላየኝ ሰው የጠላሁ ብመስልም አንተው ነህ በሀሳቤ ለኔ ግን
ከፀፀት አውጣኝ በይቅርታ ክሳለው ማረኝ የኔ ጌታ

ሩቅ ሆኜ ሳለው
ጎኔ ያለህ ይመስለኛል
እንዴት እንደምወድህ
እንዴት እንደማፈቅርህ
ማን ይረዳልኛል ያቅልኛል
ስታስበው ደሞ
የሸሸሁ ከአንተ ውዴ
እድገት ቀንቶኝ ብመጣ
አምላክ ፈቅዶ ብመጣ
አትሸሸኝም እንዴ ባክህ ውዴ

ፍቅራችንን ሳስታውስ ሳወራው ሰው መሀል
ታድያ ለምን እራቅሽው ጨካኝ ነሽ ይሉኛል
ላልቀመሰው ላላየው ማጣት ከሩቅ ቀላል
እጅ ማየት ታውቃለህ የሰው ፊት ያስጠላል
ሲጫነኝ ትዝታ ናፍቆቱ ሻንጣዬን ላነሳሳ ገና
መልሼ ፈርቼ እተዋለው ጨክኖ ይረሳኝ እልና
ንገረኝ ባክህ የኔ ገላ
ረሳህ ወይ ለመድክ ወይ ከሌላ
ካልናከኝ በቀድሞ ስህተቴ
ያንተው ናት አሁንም ህይወቴ
ሲጫነኝ ትዝታ ናፍቆቱ ሻንጣዬን ላነሳሳ ገና
መልሼ ፈርቼ እተዋለው ጨክኖ ይረሳኝ እልና
ንገረኝ ባክህ የኔ ገላ
ረሳህ ወይ ለመድክ ወይ ከሌላ
ካልናከኝ በቀድሞ ስህተቴ
ያንተው ናት አሁንም ህይወቴ×4

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists