Helen Berhe - Fitawrari lyrics
Artist:
Helen Berhe
album: Eski leyew
እህህ እህ አሃሃ
ኦሆ ሆሆ ኦሆህ
አሀ አሀሀ ሃሃ
ኦሆ ሆሆ ኦሆህ
ሳይሰስት ለራሱ
አፍቅሮኝ ከነፍሱ
ስደሰት አይቶኝ የተደሰተ
እስኪ ማን አለኝ ካላንተ
አንተ የኔን እምባ ያበስከው ከፊቴ
በፍቅርህ ሞቋል ቀዝቃዛው ቤቴ
ልመስክርልህ እስኪ በአንደበቴ
አንተ ፊታውራሪ
ከፊት የሌለብህ ዓይኔን ልቤን አብሪ
ስምህ ፊትውራሪ
ጨዋታዬን ቀዳሽ የቃላቴ መሪ
አንተ ፊታውራሪ
እጄን በእጅህ ይዘህ መንገድ አሻጋሪ
ስምህ ፊትውራሪ
በጭለማ መሀል ንጋትን አብሳሪ
ቢጠየቁ ስለአንተ እያነሱ
የኔን ያክል አይሆንም የነሱ
ቢጠየቁ ቀንና ለሊቴ
ያወራሉ ዝም ቢል አንደበቴ
ቢጠየቁ ስለአንተ እያነሱ
የኔን ያክል አይሆንም የነሱ
ቢጠየቁ ቀንና ለሊቴ
ያወራሉ ዝም ቢል አንደበቴ
አያውቁ አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
ለጠላት የምታስፈራ
ለወዳጅ የምታኮራ
መሆንህን የማያደንቁ
አንተን መሳይ አንድም አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
♪
ሳይሰስት ለራሱ
አፍቅሮኝ ከነፍሱ
ስደሰት አይቶኝ የተደሰተ
እስኪ ማን አለኝ ካላንተ
አንተ የኔን እምባ ያበስከው ከፊቴ
በፍቅርህ ሞቋል ቀዝቃዛው ቤቴ
ልመስክርልህ እስኪ በአንደበቴ
አንተ ፊታውራሪ
ከፊት የምትገኝ ዋስ ሆነህ ተጠሪ
ስምህ ፊታውራሪ
ፍቅርህን ለብሼ ተባልኩኝ ስታምሪ
አንተ ፊታውራሪ
ግርማ ሞገሴ ነህ ውበቴን ቀማሪ
ስምህ ፊታውራሪ
አንተን ስለሰጠኝ ይመስገን ፈጣሪ
ቢጠየቁ ስለአንተ እያነሱ
የኔን ያክል አይሆንም የነሱ
ቢጠየቁ ቀንና ለሊቴ
ያወራሉ ዝም ቢል አንደበቴ
ቢጠየቁ ስለአንተ እያነሱ
የኔን ያክል አይሆንም የነሱ
ቢጠየቁ ቀንና ለሊቴ
ያወራሉ ዝም ቢል አንደበቴ
አያውቁ አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
ለጠላት የምታስፈራ
ለወዳጅ የምታኮራ
መሆንህን የማያደንቁ
አንተን መሳይ አንድም አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
አያውቁ አያውቁ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist