Kishore Kumar Hits

Helen Berhe - Enat lyrics

Artist: Helen Berhe

album: Eski leyew


የዚች አለም ዝና ያልፋል እንደ ጥላ
ሀብትና ንብረትም ይቀራል ከኌላ
ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ
እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ
ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ
እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ

እንደባህር አሸዋ ልክ እንደዋክብት
በዕድሜሽ ቁጥር ላይ ቁጥር ይለቅበት
መቆምሽ ነውና እኔን የሚያቆመኝ
ባንቺ ቦታ ልዋል ህመምሽ ይመመኝ
ባንቺ ቦታ ልዋል ህመምሽ ይመመኝ
ኑሪልኝ ኑሪ
ኑሪልኝ አንቺን ያቆይልኝ
ኦ ፣ ኦሆ ፣ ዎሆ ፣ ሆሆ ፣ አሀ ሀሀ ፣ ሀሀ

የዚች አለም ዝና ያልፋል እንደ ጥላ
ሀብትና ንብረትም ይቀራል ከኌላ
ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ
እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ
ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ
እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ

ጊዜ ተገዝቶልሽ ታዞልሽ ዘመኑ
የዕድሜሽ ዳርቻ ጥልቅ ይሁን ወሰኑ
ነፃ እንዳወጣሽ አዝለሽ የኔን ቀንበር
ላንቺ ብቻ ሲባል ሞት ባይኖር ምን ነበር
ላንቺ ብቻ ሲባል ሞት ባይኖር ምን ነበር
ኑሪልኝ ኑሪ
ኑሪልኝ አንቺን ያቆይልኝ
ኦ ፣ ኦሆ ፣ ዎሆ ፣ ሆሆ
ኑሪልኝ ቆዪልኝ ቆዪልኝ
እናቴ ቆዪልኝ
ቆዪልኝ ቆዪልኝ
አንቺን ያኑርልኝ
አንቺን ያኑርልኝ
አንቺን ያኑርልኝ
ኑሪልኝ ቆዪልኝ
ቆዪልኝ
አንቺን ያኑርልኝ
ሆሆ
አሀሀ
ሀሀ
ሆሆ
ሆሆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists