Kishore Kumar Hits

Helen Berhe - Balagegn lyrics

Artist: Helen Berhe

album: Eski leyew


ባላገኝ ልቡን ባላገኝ
ባላገኝ ፍቅሩ እያሰኘኝ
ባላገኝ አልነግረው ችዬ
ባላገኝ ባጣውስ ብዬ
ከየት ይምጣ በጄ አይደል እሱ እንዴት ይሙላ ሀሳቤ
አንገቴን አውሮ ብመኝ ፍቅሩን ለማተቤ
ማማሩን ያየ ሰው መች ያዝንልኝና
በእንዳላጣህ ስጋት በገና ለገና
ልክ እንደ ባዳ ወዳጅን ማፍቀሩ
ስራዬ ሆኗል ገላህን ማለሙ
አይኔ ከአይንህ እንዳይርቅ አልነግርህ ደፍሬ
ልኑር እንዳላጣህ መውደዴን አፍኜ
ባላገኝ ባላገኝ ልቡን ባላገኝ
ባላገኝ ባላገኝ ፍቅሩን ባላገኝ
ወዳጅነቱን ከቶ ሳይነፍገኝ
ፊት ለፊቱ ቅርቡ ያድርገኝ
ባላገኝ ባላገኝ ልቡን ባላገኝ
ባላገኝ ባላገኝ ፍቅሩን ባላገኝ
ወዳጅነቱን ከቶ ሳይነፍገኝ
በዋለበት አብሮ ያውለኝ
ባላገኝ ልቡን ባላገኝ
ባላገኝ ፍቅሩን እያሰኘኝ
ባላገኝ አልነግረው ችዬ
ባላገኝ ባጣውስ ብዬ
ከየት ይምጣ በጄ አይደል እሱ እንዴት ይሙላ ሀሳቤ
አንገቴን አውሮ ብመኝ ፍቅሩን ለማተቤ
ማማሩን ያየ ሰው መች ያዝንልኝና
በእንዳላጣህ ስጋት በገና ለገና
ባለመናገር ቢቀርም ያሰብኩት
ቢከፋብኝስ ምላሹን ፈራሁት
አብሮኝ ካለ ሁሌ ካልጠፋሁ ከፊቱ
ወንድም ሆኖኝ ይኑር ይቅር ባልነቱ
ባላገኝ ባላገኝ ልቡን ባላገኝ
ባላገኝ ባላገኝ ፍቅሩን ባላገኝ
ወዳጅነቱን ከቶ ሳይነፍገኝ
ፊትለፊቱ ቅርቡ ያድርገኝ
ባላገኝ ባላገኝ ልቡን ባላገኝ
ባላገኝ ባላገኝ ፍቅሩን ባላገኝ
ወዳጅነቱን ከቶ ሳይነፍገኝ
በዋለበት አብሮ ያውለኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists