Kishore Kumar Hits

Helen Berhe - Enawra lyrics

Artist: Helen Berhe

album: Eski leyew


እህህ
እህህ
አሀሀ
እህህ
አሀሀ
የሰው አፍ ማነው የሰማ እኔ ነኝ ወይስ አንተ
ምክንያቱ ሳይታውቅ ውስጣችን የጎደለ
እንዳላጣህ እፈራለሁ ፍቅሬ አውራልኝ ያስከፋህን
ተነጋግረን እንመካከር የሰማሀው ምንም ይሁን
የሰው አፍ ማነው የሰማ እኔ ነኝ ወይስ አንተ
ምክንያቱ ሳይታውቅ ውስጣችን የጎደለ
እንዳላጣህ እፈራለሁ ፍቅሬ አውራልኝ ያስከፋህን
ተነጋግረን እንመካከር የሰማሀው ምንም ይሁን
አጥፍቻለሁ ብዬ ተሰምቶኝም አይደለ
ለኔ ልክ መስሎኝ ያስከፋህ ነገር ካለ
እንድንግባባ እንጂ ማኩረፍህ ሲበዛብኝ
መሳቅ አመልህን ሳላውቀው ምን ነካብኝ
ሰበብ ፈጥሬ ሳኮርፍ ሁሉን ቻይ አበባዬ
ንፋስ ሲነካኝ አዝነህ ብትደርብ በገላዬ
ምን አስከፋህ ሰሞኑን ከወዴት ነው ቸልታው
እንዳይቆይብኝ ፍቅሬ ይቅርብኝ ይህ ዝምታው
እህህ
እህህ
አሀሀ
እህህ
እህህ አ

የሰው አፍ ማነው የሰማ እኔ ነኝ ወይስ አንተ
ምክንያቱ ሳይታውቅ ውስጣችን የጎደለ
እንዳላጣህ እፈራለሁ ፍቅሬ አውራልኝ ያስከፋህን
ተነጋግረን እንመካከር የሰማሀው ምንም ይሁን
የሰው አፍ ማነው የሰማ እኔ ነኝ ወይስ አንተ
ምክንያቱ ሳይታውቅ ውስጣችን የጎደለ
እንዳላጣህ እሰጋለው ፍቅሬ አውራልኝ ያስከፋህን
ተነጋግረን እንመካከር የሰማሀው ምንም ይሁን

የራስ ሰው ሲከፋው ዝም ይላል ከተከፋ
እስኪያልፍለት ድረስ ንዴቱም እስኪጠፋ
በዛብኝ በዛብኝ ከብዶኛል ይህ ፀጥታ
ተጣልቶኛል ቤቴ እሚደምቀው በፈገግታ
ሰበብ ፈጥሬ ሳኮርፍ ሁሉን ቻይ አበባዬ
ንፋስ ሲነካኝ አዝነህ ብትደርብ በገላዬ
ምን አስከፋህ ሰሞኑን ከወዴት ነው ቸልታው
እንዳይቆይብኝ ፍቅሬ ይቅርብኝ ይህ ዝምታው
እህህ
እህህ
አሀሀ
እህህ
አሀሀ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists