Kishore Kumar Hits

Nhatty Man - Yemenor lyrics

Artist: Nhatty Man

album: Vol ፫


የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
የህይወት ጎዳና የት እንደሚያደርስህ አታውቅምና
መልካም ግበር እስካለህ በእድሜ በጎ ሚና
መኖር ይችል እንደው በፍቃዱ አያስተውል ምነው
ለጢቆ እድሜው ሰው ይፋጃል መቶ ለማይሞላው
የራስ መልክ ወዳጁን ሰውን እየገፋ
ለነፍስ አድራለው ሚል ለቁርጥ ቀን ተስፋ
እርባና ቢስ ከንቱ መና ነው ትጋቱ
ቅንነት ካልታየ በህይወት በእውቀቱ
ፅድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም
እረፍትን ችሮ የሚያኖር በፍቅር በሰላም
በጎ እያለ ክፋት አያዋጣም
የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
አትታበይ አትመካ አለኝ አትበል ከእጄ
ህይወት የት እንደምጥልህ አታውቅም ወዳጄ
አትታበይ አትመካ አለኝ አትበል ከእጄ
ህይወት የት እንደምጥልህ አታውቅም ወዳጄ
የሰው ልጅ ሆነ ክንቱ
ከፍቅሩ በዛ ጥፋቱ
በላዩ ቁስ አንግሶ
ከክብሩ ራቀ ጨርሶ
አክሊሉን አውልቆ ጣለው የክብር ሽልማቱን
ከግርማው አንሶ ጥፋቱ ብሶ ገፋ ዙፋኑን
ቀልቡን ገዝቶ ላስተዋለው
መልካምነት ለራስ ነው
ቀልቡን ገዝቶ ላስተዋለው
ታዞ መኖር መልካም ነው
የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
የሚኖር በምድር ላይ አንዴ ነው
ክፉ ማሰብህ ምንድን ነው
(ለአጭር እድሜ)
(ለአጭር ህይወት)
(ለአጭር ለአጭር)
(ለአጭር እድሜ)
(ለአጭር ህይወት)
(ለአጭር ለአጭር)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists