Nhatty Man - Atansim lyrics
Artist:
Nhatty Man
album: Man
ምን እንደምል ከበደኝ ማየት ያለፈዉን
አረ ለምን አቃተኝ ማሰተዋል መጪዉን
ዛሬ እንዲህ ሆነህ እያየዉህ በአይኔ
ማለፍ ሲያሳዝነኝ እንደማላዉቅህ ያኔ
ግን አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
ኑሮ ባይደላ ባይኖርህ ከእጅህ ላይ
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አትዘን አትከፋ ለአንተም አለህ መጽናኛ
በክፉ ቀን ደራሽ የማይርቅ የማይጠላ
ተወዉ በቃ ተወዉ ሁሉም ያልፋል እንደ ትላንት
ማጣትህን እንጂ ዉስጥህን ማን አይቶት
ኦህኦ ኦህኦ
♪
ሳልፍህ ኖርኩኝ ሳገልህ ክብርህን ዘንግቼ
ቀን ሲጥልህ ራኩ እኔም ሰዉነትህን ክጄ
በደጉ ዘመንህ አለሁ ባይ ባይጠፋም
አንተ ግን አንተዉ ነህ ጊዜዉ ቢሄድ ቢለወጥም
ግን አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
ኑሮ ባይደላ ባይኖርህ ከእጅህ ላይ
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
የቅርብህ እሩቅ ሆኖ ቢሸሽህ ቢለይህም
ተወዉ አታቀርቅር ቢክድ ቢለወጥም
ታዉቃለህ ለራስህ ባይተርፍ ባይደላህም
እመን በቃ አትዘን ከማንም አታንስም
ግን አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
ኑሮ ባይደላ ባይኖርህ ከእጅህ ላይ
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
(ኑሮ) ኑሮ ባይደላ ባይኖርህ ከእጅህ ላይ
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
አንተ ከማንም አታንስም አታንስም
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist