Kishore Kumar Hits

Nhatty Man - Salayish lyrics

Artist: Nhatty Man

album: Man


ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ
ካላየሁሽ ይጨንቀኛል ይከፋኛል
እንዲያው ዝም ብሎ ሆድ ይብሰኛል
ካልቻልሽ አንቺ እኔው ልምጣ ልምጣ ልይሽ
ከሚያሽጨንቀኝ ብሶ ናፍቆትሽ
ሳላይሽ አልውልም አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለው ናፍቀሺኛል አይሻለው
ካላየሁሽ ይጨንቀኛል ይከፋኛል
እንዲያው ዝም ብሎ ሆድ ይብሰኛል
ካልቻልሽ አንቺ እኔው ልምጣ ልምጣልይሽ
ሀሳብ ጨረሰኝ ብሶ ናፍቆትሽ
ሳላይሽ አልውልም አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለው ናፍቀሺኛል አይሻለው

አዲስ አመል ያነጫንጨኛል
ካላየሁሽ ደርሶ ይከፋኛል
ህመሜን ማን አውቆት የኔን ጭንቀት
ነገር ላይጥመኝ አንቺ የሌለሽበት
ሳቅ ጨዋታሽን ለምጄው ይናፍቀኛል
ያንቺን ባላውቅም ለኔስ አንቺን ያሰኘኛል
ሰው ናፍቄ ችዬ እንዴት ዝም'ላለው
ሰበብ ፈጥሬ በምክንያት አይሻለው
ሳላይሽ አልውልም አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለው ናፍቀሺኛል አይሻለው

ለብቻው ነው የኔስ ጉዳይ አንቺን ሳጣ
ከሰው አልገጥም ቃል ካፌም አይወጣ
ይባስ ብሎ ደርሶ ይከፋኛል
ፍቅርሽ ሃይሎ አመሌ ሸሽቶኛል
ሳቅ ጨዋታሽን ለምጄው ይናፍቀኛል
ያንቺን ባላውቅም ለኔስ አንቺን ያሰኘኛል
ሰው ናፍቄ ችዬ እንዴት ዝም'ላለው
ሰበብ ፈጥሬ በምክንያት አይሻለው
ሳላይሽ አልውልም አይሆንም አልቀርም
ካለሽበት እመጣለው ናፍቀሺኛል አይሻለው

ሆ ሆ ሆሆ
ሆ ሆ ሆሆሆ
ሳላይሽ አልውልም አይሆንም አልቀርም
ካልሽበት እመጣለው ናፍቀሺኛል አይሻለው
ሳላይሽ አልውልም አይሆንም ኧረ አይሆንም
ካልሽበት እመጣለው ናፍቀሺኛል አይሻለው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists