እሹሩሩ ማሙሽ እሹሩሩ
ልጄ እሹሩሩ ማሙሽ እሹሩሩ
እሹሩሩ ማሙ እሹሩሩ
ልጄ እሹሩሩ ማሙሽ እሹሩሩ
ስበላም አዝዬህ ስጠጣም አዝዬ
ስራመድ አዝዬህ እንዳይከፍህ ብዬ
ስበላም አዝዬህ ስጠጣም አዝዬ
ስራመድ አዝዬህ እንዳይከፍህ ብዬ
እንዲህ ትለኝ ነበር እማ
ከእንግዲህ ማን አለኝ እናት
ከእንግዲህ ማን አለኝ አባት
አ ሲርበኝ አ ሲጠማኝ
አለዉ ብሎ የሚያፅናናኝ
ከእንግዲህ ማን አለኝ እናት
ከእንግዲህ ማን አለኝ አባት
አ ሲርበኝ አ ሲጠማኝ
አለዉ ብሎ የሚያፅናናኝ
የእናትነት ፍቅሯ ከልቤ ዉስጥ ገብቶ
ትሄዳለች ብዬ ሳላስበዉ ከቶ
ሄደች እስከወድያኛዉ ዳግም ላትመለስ
የእናትነት ፍቅሯን ጠግቤ ሳልጨርስ
አንድ እሷ ነበረች ለኔ ተቆርቋሪ
ለሀዘን ለደስታዬ ለችግር ተጠሪ
አሁን ም ልሁነዉ ምንስ ይዋጠኝ
ምስኪኗን እናቴ ሰቶ ሲነሳኝ
ይሁና ይሁና ይሁና ይሁና
አምላክ ያመጣዉ ነዉ ሞት አይቀርምና
ይሁና ይሁና ይሁና ይሁና
አምላክ ያመጣዉ ነዉ ሞት አይቀርምና
ከእንግዲህ ማን አለኝ እናት
ከእንግዲህ ማን አለኝ አባት
አ ሲርበኝ አ ሲጠማኝ
አለዉ ብሎ የሚያፅናናኝ
ከእንግዲህ ማን አለኝ እናት
ከእንግዲህ ማን አለኝ አባት
አ ሲርበኝ አ ሲጠማኝ
አለዉ ብሎ የሚያፅናናኝ
እባክህ አምላኬ አስብላት ለሷ
እኔን ይቆርቁረኝ ድንጋይ ነዉ ትራሷ
ሄደሻል እናቴ አንዱንም ሳትይዢ
ጉርጓዱን ሰፋ አርገሽ ለኔም ቦታ ያዢ
ስማኝ አምላኬ ሆይ የምለምንህን
ዉለታ ዋልልኝ ተቸገር ለሚስኪን
እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ እንደነ አብርሃም
አኑርልኝ ነብሷን በገነት ዘላለም
ይሁና ይሁና ይሁና ይሁና
አምላክ ያመጣዉ ነዉ ሞት አይቀርምና
ይሁና ይሁና ይሁና ይሁና
አምላክ ያመጣዉ ነዉ ሞት አይቀርምና
ይሁና ይሁና
ይሁና ይሁና
አምላክ ያመጣዉ ነዉ
ሞት አይቀርምና
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist