Haile Roots - Yetefa Yigegnal lyrics
Artist:
Haile Roots
album: Chiggae
የጠፋ ሲገኝ አውቃለው
የተከፋም ስቆ አያለው
የደነቀኝ ግራ የገባኝ
ጠፍቶ ሚሆን አንድም አፅናኝ
ተስፋ ላጣ ለጨነቀው
ምን ሊበጅ አበቃ ሚለው
ካላለ አለ ዙሪያው ያለ
ነገ መልካም የተሻለ
ተናዶ ማልዶ ማቆ ጠቁሮ ከሳ
ጤናው ጠፍቶ ልቡን ነሳ
አትበሉ ተውት ይዳን እስኪነሳ
የማትጠቅሙት ሽሹ ከዛ
ሰው ባለም ክፉ ደጉን አልፎ ሊያየው
የተሰጠው ተስፋ ሳለው
ስለምን አዛኝ መስሎ ይመክረዋል
ባይዞህ ፋንታ አበቃ ይለዋል
የጠፋ ሲገኝ አውቃለው
የተከፋም ስቆ አያለው
የደነቀኝ ግራ የገባኝ
ጠፍቶ ሚሆን አንድም አፅናኝ
ተስፋ ላጣ ለጨነቀው
ምን ሊበጅ አበቃ ሚለው
ካላለ አለ ዙሪያው ያለ
ነገ መልካም የተሻለ
ተጨንቆ ላለ ልቡ ለተከፋ
ፈውስ የሚሆን አዲስ ተስፋ
ካልሰጠው ምን ሊጠቅመው ዙሪያው ያለው
ውስጥ ህመሙን ላይፈውሰው
የሆነ ሀቀኛ ሰው ብርቱ ልቡም
ሀይል የሚሆን ለወዳጁም
አይልም አበቃልህ ለጨነቀው
ለሚናፍቅ ነገን ሊያየው
የጠፋ ሲገኝ አውቃለው
የተከፋም ስቆ አያለው
ተስፋ ላጣ ለጨነቀው
ምን ሊበጅ አበቃ ሚለው
የጠፋ ሲገኝ አውቃለው
የተከፋም ስቆ አያለው
ተስፋ ላጣ ለጨነቀው
ምን ሊበጅ አበቃ ሚለው
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist