Kishore Kumar Hits

Rophnan - Qal lyrics

Artist: Rophnan

album: Sidist (VI)


ልናገር ከመሸው ልደር
ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር
ልናገር ከመሸው ልደር
ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር
አልኩና ቃሌን ፈራሁ እንደገና
ቃል ሰው ይሰብራልና
ቃሌን ፈራሁ እንደገና
ቃል ሰው ይገድላል
ቃል ነበረ ከራስ መከረ
በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ
በፈጠረው ሰው ቃል አደረ
ሰው ግን በአፉ ቃል ሰው ገደለ
ቃል ነበረ ከራስ መከረ
በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ
በፈጠረው ሰው ቃል አደረ
ሰው ግን በአፉ ቃል ሰው ሰበረ
ሰው የቃል ስራ
በቃል እጅ የተሰራ ስጋው
ነው የቃል ጥራዝ
በቃል አፍ የወጣ ነው ነፍሱ
ሰው የቃል ትንፋሽ
ህይወትም በኃይለቃል የበራች ናት የቃል ኩራዝ
ከፀሐይ ከሰማይ ቃል ከቀደመ ከዓለም
እንግዲህማ እውነቱ ከቃል በላይ ኃይል የለም
ሰውም በተሰጠው ቃል ዓለምን ሁሉ ያጠፋል
በሰው ያደረው ግን ቃል ዓለምን ደግሞ ያድናል
አጀብ
በዚህች ዓለም ሰውን የሚያነሳ ሰውን የሚጥል
እንደ ቃል የለም
ሰው በአፉ ቃል ሰውን ልክፍ ዓለም ጥምም
ሰው በቃሉ መልካም ቢጽፍ ምድር ቅንን ቀና
አጀብ በቃል ዓለም
ሰው ባያውቀው የአንደበቱን የአፉን ቀለም
ፈጣሪ ቃል በሰው ገላ እንዳደረ
ሰው መልሶ በሰው ቃል ሰው ገደለ
(ሰው ገደለ)
ልናገር ከመሸው ልደር
ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር
አልኩና ቃሌን ፈራሁ እንደገና
ቃል ሰው ይገድላልና
ያ ደሃ ያ የሃብታም ቤቱ ዘበኛ
ሲጠብቅ ቀንና ሌት የማይተኛ
ላስተዋለ ልብ ላለ ላወቀው
ያን የሃብታም ቤት ሳይሆን
ቃሉን ነው የጠበቀው
እኮ ቃል አይደለም ወይ መጀመሪያ ማንስ ነበረ?
ቃል አይደለም ወይ የፈጠረ ሰማይ ከምድርን?
ቃል አይደለም ወይ የወረደ ከድንግል ሊያድር?
ቃሌን ብፈራው አይደለም ወይ ፈሪሐ እግዜር?
ቃል ነበረ ከራስ መከረ
በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ
በፈጠረው ሰው ቃል አደረ
ሰው ግን በአፉ ቃል ራሱን ገደለ
የአፉን ያወቀ እግዜርን ከነፍሱን አስታረቀ
ለእውነት ከአፉ ያፈለቀ
የህይወት ፍሬን ዘርቶ አፀደቀ
ሰው ቃሉ እንጂ የበላው
ሆዱ ገነት ላያገባው
ንጥቂያው ወይ ቅሚያው እኔ ልናገር ሽሚያው
ላንወጣ ከማጡ የሚሉት ላያጡ
ጣቶች አፍ አወጡ ፖስት ቃል ሳይመርጡ
አፍ በዛ ቃል ጠፋ ፍቅር አንሶ ሆድ ከፋ
ሁሉም አወቅኩኝ አለ ቃል ረክሶ ታች ሆነ
ልናገር ከመሸው ልደር
ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር
የአንገቴን ክር ቃሌን አልፎ ላይገዛው ብር
ከእውነት ዛፍ ስር እንኳን ሰው በቃሉ ያድራል ትል
ጊዜም ዘመነ ደመረ ጨመረ አፍም ከአደባባይ ዋለ
ቃልም ባከነ ፈጠነ ቀጠነ ሰው ወርዶ በፌስቡክ ማለ
ዘመነ ስልክ ዘመነ ስማርት ዘመነ ታይፕ ዘመነ ጣት
ዘመነ ላይክ ነው የላይክ ጥማት
መስታወት ላይ የውሸት መዐት
መስታወት ዋሸ መስታወት ዋሸ
መስታወት ዋሸ መልክ አመለክን በፊልተር የታሸ
መስታወት ዋሸ በጊዜው መስታወት ዋሸ
የሃገር ሰው መስታወት ዋሸ
ቃል እሸጥ ብሎ በቁሙ ሰው ቃዠ
መስታወት መስታወት አየ
የመስታወት ዝና በመስታወት ናኘ
የመስታወት መልኳን በመስታወት ዳኘ
የመስታወት ቃል ተሰብሮ ተገኘ
ገበያ ገበያ ቃልን እንደ ሸቀጥ
ቃል ከሚሸጥበት
ውሃ ሲገድል ቀድሞ ያስቃል
የሰው ልጅ አፍ ከባሕር ይጠልቃል
ኢሞጂ ኢሞጂ ከአንገት በላይ
ልከን ተወሻሽተን ግን በዓይን ላንተያይ
ቆይ ቆይ በየት?
ቆይ ቆይ በየት? በየት?
ኢሞጂ ኢሞጂ ከአንገት በላይ
ወደድኩሽ ይላታል ልብ ልኮ ልቧንም ሳያይ
ቆይ በየት?
ቆይ በየት? በየት?
ልናገር ከመሸው ልደር
ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሁሉም ቢቀር
ልናገር ከመሸው ልደር
ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር
አልኩና ቃሌን ፈራሁ እንደገና
ቃል ሰው ይሰብራልና
ቃሌን ፈራሁ እንደገና
ቃል ሰው ይገድላልና
ቃል ነበረ ከራስ መከረ
በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ
በፈጠረው ሰው ቃል አደረ
ሰው ግን በአፉ ቃል ሰው ገደለ


ይሁን ለኔ ትውልድ
ፎፍናን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists