Kishore Kumar Hits

Rophnan - Desse lyrics

Artist: Rophnan

album: Sidist (VI)


ደሴ መጀን

ብለን ሞተናል
ውድ ለብሰናል

አመት ደርሰናል
ወርቅ ለብሰናል

እስኪ በይ እስኪ
ከፍቅርሽም አስነኪኝ
ነይ አይናለሜ
አንቺ ካለሽ ሁል ግዜ ቀኑ
በዓል ነው
ጠቡም ሰርጋም ክፉም ውጪ
ዳር ነው
ያልጣፈጠኝ ኮሶ እሬቱም
ማር ነው
ካንቺ የሚለየኝ ኧረ ማነው
ተይ ማነው?
ተራራው አምባሰል
ሀገሩም ደም ደሴ
ሀገሩም ቆቦ
ውሃም ከሚሴ
ውሃውም ሐይቅ ነው
ውሃውም ገራገር
እኔ የከተማ ሰው
መሃል ሀገር ሸገር
በሸገር ሸገር
ምን አለ በሸገር
ሀገር ስጠኝ ካልሺኝ
ዋ ብዬሽ እንዳልቀር
ዋ ብሎኝ የቀረው ልጅ
ብለሽ ብታሚኝ
ሀገር ያውቃል አንቺም
ደሴን አትሰጭኝ
Jaallee koo
Qabii laphee koo
Garaa koo
Beektaa qalloo koo
Jaalalti kee damma
Dammee ko
Taate yaada koo
Taate maarree
Takkittii kan koo
Qubee koo
Afaan koo
እስካገኝሽ ሳልምሽ
ካንቺ በር ደርሼ እንዳልስምሽ
ወግ አይደለም በሀገር ሳልክስሽ
ጥሎሹን ሳልችልሽ
ወርቅ እንደ ጃኖ ሳልደርብሽ
እኔን ልሸልም አይደለም ወይ
ለምነው ምትይኝ ቆይ
ምትግደረደሪው
መውደድሽ እንድ እርቦኝ
ሰሚ እንኮይ
የፍቅር ሀገር ደሴ አይደለም ወይ

ብለን ሞተናል
ውድ ለብሰናል

አመት ደርሰናል
ወርቅ ለብሰናል

እስኪ በይ እስኪ
ከፍቅርሽም አስነኪኝ
ነይ አይናለሜ
አንቺ ካለሽ ሁል ግዜ ቀኑ
በዓል ነው
ጠቡም ሰርጋም ክፉም ውጪ
ዳር ነው
ያልጣፈጠኝ ኮሶ እሬቱም
ማር ነው
ካንቺ የሚለየኝ ኧረ ማነው
ተይ ማነው?
Low low low low
ዝቅ ዝቅ ዝቅ
ደግሞ ከፍ
ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ
መልሽ መልሽ
ደሞ
Low low low low
ዝቅ ዝቅ ዝቅ
ደሞ ወደላይ
ከፍ ከፍ ከፍ
መልሰኝ
የሀገሬ ሰው ሸላይ ነው
ይታያል ገና
ደሴ ላይ ደስ አለኝ አገኘሁ መላ
ውብአለም ይላታል ለቤቷም ጥላ
በይልኝ ዘና ደና
ጥርሷም ይረቃል
ጉራማይሌ ንቅስ ያንፀባርቃል
እስክስ ይደቃል
ካንገቷ ንቅል አይኗም ይሰርቃል
ከተራራው ጠፍ
ከቤተመንግስት ቆሜ አይጠየፍ
ባየው ከሚሴን
በንጉሥ ፈረስ ደሴ ላይ ከተፍ
ሚካኤል ንጉሥ አለች
ሰርቃ ብታየኝ ደንግጣ በስሙ ማለች
በእሪኩም የተሳመች
የመልኳ ሳያንሳት ማርዳዋን በአንገቷ አዋለች
ምን ታየኛለህ አቦ
በል እሪኩም
ግጠመኝ ያዝ አትቁም
ደሴ ገራገር አለም ባቲ አምባሰል
ስጠኝ የውበት ጥጉን
ላሊበላ ልሳለም እመጣለሁ ገና አዬ
ወሎ መጀን
ሰላምሽ ይብዛ ይልሻል ሮፍናን
እዬዬዬ
ወሎ መጀን

ደሴ መጀን
ወሎ መጀን

ደሴ መጀን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists