Kishore Kumar Hits

Rophnan - Yeamangu Quine lyrics

Artist: Rophnan

album: Sidist (VI)


አማኝ ተስፋን ከፈጠረው አገኘ
ተስፋን ይዞ አማኝ ቅኔን ተቀኘ
ቅኔን ዘርፎ አማኙ ስሙ ናኘ
ሮፍናን በአምላክ ብቻ ተዳኘ
እያመነ ሌቱን ሰጥቶ እያደረ
በይቅርታው ዙሪያው በቸር ታጠረ
ያጠፋል ግን እንደ አባቱ ዋለ
ሮፍ- ናን!
የአማኝ ሴት ቅኔ
ይመጣሉ!
አንድ ሁለት አንድ ሁለት
ውሸት ግን መሳይ እውነት
ይሄዳሉ!
ለብሰው ሰናይ ጥለት
ታማኝ መሳይ ክህደት
መሽቶ እስኪነጋ-!
መስሎ የተጠጋ
ክፍት የተዘጋ
ላላወቀው-!
ያዝ በለው ያዝ ያዝ
ያዝ ያዝ ያዝ አንተ!!!
ያዝ ከታመቀው (ያዝ!)
ጥበብ ከሰበቀው (ያዝ!)
እውነትን ካወቀው ጠበል እርሱ ካፈለቀው (ያዝ!)
ሦስቱን ዓይን አሻግሮ ከራስ ከታረቀው (ያዝ!)
በጥቁር ገላ ጥቁር ክር "ቶ" መስቀል አጥልቀው ከእርሱ እንዳትርቅ!!!
የእናና ግንባር ያወራል
"ቶ" መስቀል ከፀሐይ ያበራል
የግንባሯን ኩል ንቅሳት ምክንያቱን ላወቀው (ያዝ!)
ያዝ በለው ያን የሰው ጥሬ (ያዝ!)
በል ፍታ የአማኙን ቅኔ
ከላይ ቃል ከላይ ምት
ከላይ ጣል ከላይ ስንት
ከላይ ሰጠኝ ከላይ ስንቅ
ከላይ ጥበብ ከላይ ጥንት
ከላይ ካለው የላይ ድንቅ
በላይ ኃይሉ የላይ ጥግ
ሰው ከእርሱ እንዳትርቅ!!!
ባመነው
ሰው በእምነቱ ልክ ሊያገኝ ግድ ነው
የታመነ ድንጋይ ዋጋው ወርቅ ነው
የእጁ አይደለም የእምነት ፍልፍል ነው
ቤ‐ተ‐ስ‐ኪ‐ያ‐ኑ‐ን ላየው!
የአማኙ ቅኔ
አንድ አማኝ ያለው ብርሃን
ለሺህ ትውልድ ይበራል
የአማኙ ቅኔ
ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
ነገን አልፎ ሊነበብ
የአማኙ ቅኔ
የአማኙ ሰው ቅኔ
ደርሷል ለዘመኔ
የአማኙ ቅኔ
ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
ነገን አልፎ ሊነበብ
የአማኙ ቅኔ ከፍ
ማን ብሎ ጠራው ስሜን?
ሮፍ‐ናን
አውቋል ልቤ
ብሎ ከፍታ ላይ ነቅቷል ሳልሣዊ ዓይኔ III
አመስጋኝ ነኝ ለእነርሱ
ብራና ፍቀው የእውቀትን ብርሃን ላነሱ
ብርሃን ለራቀው ሰው ቆመው ጾመው ለከሱ
ድንጋይ እንደ ቅቤ ቆርጠው ቤቱን ላነፁ
ድንጋይ የሆነን ልብ መክረው ዘክረው የመለሱ
"ቶ"
ይላል የመቋሚያው ላይ አናት "ቆ"
ሳብዕ ቀስተደመና ቀለማት "ቆ"
ቤዛ ሚስጥረ ፊደል እናት "ቶ"
"ቆ" ሮ- ፍናን!
ገረዓልታን አስተዋለ ፅናቱስ ከየት ነው አለ
ገረዓልታን የፈለፈሉ እጆች በማይሻር ጥበብ የተካነ
ገረዓልታን የሚወጡ እግሮች እንደሰው አይደክሙም እርሱ እስካለ
እምነቱን በእርሱ የጣለ የማይቻለውን ሆነ
ሆነ!
እምነት ይዞ በምድር ጉዞ ቀንና ለሊቱን ጣረ
ከማይታፈስ ከማይደረስ ከሚመስለው ጫፍ ላይ ዋለ
ፅናትን እምነትን ችሎ መገኘትን ከአማኙ ቅኔ ተማረ
አመነ! ልቡ ተካበ! ገረዓልታ ሆነ!
አቦይ ቀሺ!
ጎይታ ምህረይ!
የአንተ ፅናት ከዘመን ዘመን እያስተማረኝ
የአንተ ኪነት ከላይ የመጣው ተስፋ እየሆነኝ
ሰው አደረገኝ
ከሰው ደመረኝ
ጧፍም በጧፍ ይበራል
ሰውም ሰው አይቶ ይፀናል
የአንድ አማኝ ጸሎት ሃገር ያክማል
የአማኙ ቅኔ
አንድ አማኝ ያለው ብርሃን
ለሺህ ትውልድ ይበራል
የአማኙ ቅኔ
ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
ነገን አልፎ ሊነበብ
የአማኙ ቅኔ
የአማኙ ሰው ቅኔ
ደርሷል ለዘመኔ
የአማኙ ቅኔ
ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
ነገን አልፎ ሊነበብ
የአማኙ ቅኔ-!

የአማኙ ቅኔ!
የአማኙ ቅኔ!

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists