Kishore Kumar Hits

Rophnan - Sew neh yilal lyrics

Artist: Rophnan

album: Sost (III)


የሀገሬ ልጅ
ስም አገኘሽ ወይ?
የሀገሬ ልጅ
ማነኝ አልሽ ይሆን?
እኔስ ልቤ እውነት አየ
ማን እንደሆንኩኝ ለየ
ነህ የተባልኩት እንዲገባኝ
ኋላዬን ዞር ብዬ ብቃኝ
ስሜ ተፅፎ አየሁት በክብር ቃል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ከቋንቋ በፊት
ከዘር ቀድሞ ተፅፏል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ከሀይማኖት ባህል
ከእምነትም ይቀድማል
ሰው ነህ ይላል
ቀድሞ ሥላሴን ሸዋ ምኒልክ ቴዎድሮስ ሳይደግም
ግራኝ ሳይከትም ጉዲት ሳትጥል በቁም አክሱምን
ቀድሞ ቢላልን ቀድም አዛንን ነብይ መላኩን
ቀድሞ ያሬድን ሦስቱ ዝማሬን በልጅ መዳንን
ንግስተ-ሳቢት ሳትይዝ ስንቋን ለሲና ሚሆን
ሳትጓዝ ልታይ የአምላክን ስራ ጥበብ ሰለሞን
ጠቢቡም ሳይዘምም
ምኒልክ ሳይቀድም ፅላት ሳይከተል
ከሁሉ በፊት በሀገሬ
ኧረ ማን ነበር አለሜ
ጦቢያ እናት አለም የአለም ብርሃን
ጊዮን ሚዞርሽ የነፍስ እጣን
ሙሴ ለዮቶር ልጅ የበቃብሽ
ቅድሚያ እሱ ነፃ የወጣብሽ
ምድርም ታሪኳ ቢዘረጋ
ሀ ብሎ ሚጀምር ዘፍጥረት አንቺ ጋር
እምነት ታሪኳ ቢፃፍላት
በአንድነት ተገኙ ናጋሺ እና ፅላት
ዛሬ አንተ ሰው ማነህ አንተ ሰው ማነህ
ብለው ጠየቁኝ
የማነኝ ልበል ከአንቺ መፈጠር ብዙ አድርጎኝ
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ማገር ነው የአባት ቤት ይመታል
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ሰው መሆን የአባቱ ይበቃል
የሀገሬ ልጅ
ስም አገኘህ ወይ?
የሀገሬ ልጅ
ማነኝ አልክ ይሆን?
እኔስ ልቤ እውነት አየ
ማን እንደሆንኩኝ ለየ
ነህ የተባልኩት እንዲገባኝ
ኋላዬን ዞር ብዬ ብቃኝ
ስሜ ተፅፎ አየሁት በክብር ቃል
ሰው ነህ ይላል
የእናቴ መቁጠሪያ ዞር ዞር
የወጣው ልጇ ሰላም ጤና እንዲሆን
በይ እናት አለም
ፀሎትሽን ከእኔ ላይ ቀንሰሽ ለኢትዮጵያ አድርጊ
እኔ እንድኖር
አለዚያማ
ቢደርስልኝ የአንቺ ፀሎት እማ
ለብቻዬ ያለ ሀገርእማ
አልኖርማ
አንቺ ያየሽውን አላይእማ
እውነት እውነት
ፀሎትሽ ላይ ሀገር ጨምሪበት
የኔ ትውልድ ሰው እንዳይሆንበት
አጎንብሶ ሄደ ከአንገትና ጀርባው ዘር ጭነውበት
አይቼ እንዳላየሁ ሆድ ከሀገር ይሰፋል ብዬ እያለፍኩት
ማነህ ብለው እነ ሆድ ከሀገር ይበልጣል ልቤን አስጨነቁት
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ማገር ነው የአባት ቤት ይመታል
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ሰው መሆን የአባቱ ይበቃል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ሰው ነህ ይላል
ባለሀገርነት ይህ ነው
ሠው ሀገሩ እግዚአብሔር ነው
እግዜር ሀገሩ ፍቅር
ፍቅር ግን የለው ሀገር
ፍቅር ሳይኖረው ሀገር
ሀገሬ አንቺን ሳፈቅር
የፈጠረኝ እንዳለው
ሠው አታደርጊኝ ምነው
የፍቅር ቃል አያልፍ ዘንድ አለም ያልፋል
ከአንቺ በፊት ነበር ስሜ ሠው ነህ ይላል
ፍቅር ሳይኖረው ሀገር
ሀገሬ አንቺን ሳፈቅር
ለፍቅር ቦታ ከሌለሽ
ከበር እግዜርን መለስሽ
እግዜርን መለስሽ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists