Zeritu Kebede - Degu Abate lyrics
Artist:
Zeritu Kebede
album: Atihidibign
መልካም አባት ነበርክ ለኔ አያጠራጥርም
እንደ ልጅ የሚገባኝን አልከለከልከኝም
ግን ስላንተና ስለሷ ሳስብ ይከፋኛል
ምን አይነት ጨካኝ ሰዉ ነበርክ ያሰኘኛል
♪
እንዳልዘምም አድራጊዬ
እንዳልጠፋ ጠባቂዬ
እንዳትቆይ አልደላሃት
እንዳትሄድ በኔ አሰርካት
ያልሆንክልኝ ነገር የለም አባቴ ለልጅህ
ገርተህ አሳድገኀኛል እዉነት አስተምረህ
ግን እንዴት እንዴት አድርጌ ልርሳዉ በደልህን
የአይን እማኝ ነበርኩኝና ሲከፋት ሚስትህን
♪
አድራሽ መላሽ አገልጋዬ
መምህሬ መጋቢዬ
ስትታመን ያልታመንካት
ስታከብርህ ያዋረድካት
አሀ አሀ አሀሀሀሀሀ
አሀ አሀ አሀሀሀሀሀ
በምን ሀጥያቷ በየቱ በደሏ
ቀጣፊ አጭበርባሪ ዉሸታም መባሏ
ሸንጐ ታምኝ ሆኖ ለአንተ ከሷ በላይ
ስትጠቁር ስትነክሳት ደግነትዋን ሳታይ
ስለኔ ስትችልህ ከፋኝ መበደሏ
ለምን ደግ አባቴ ለሷ ክፉ ባሏ
ለለ ለለ ለለለለ
ለለ ለለለለ
ለለ ለለ ለለለለ
ላለላ ላለ
ለለ ለለ ለለለለ
ለለ ለለለለ
ለለ ለለ ለለለለ
ላለላ ላለ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist