Kishore Kumar Hits

Zeritu Kebede - Yenem Ayin Aytoal lyrics

Artist: Zeritu Kebede

album: Atihidibign


አንዱን ሊያድነው አንዱን ሊያሞኘው
ካንዱ በፈሰሰው አንዱን ሊያርሰው
ላዘነው ሰው ምነው ቢያካፍለው ቢያቻችለው
ለተረፈው ምነው በቃህ ቢለው ይብቃህ ቢለው
አንዱ በዝቶበት ሲቸገር መምረጥ
ሌላው ምንም አጥቶ ላይታች ሲራወጥ
ላዘነው ሰው ምነው ቢያካፍለው ቢያቻችለው
ለተረፈው ምነው በቃህ ቢለው ይብቃህ ቢለው
ለመኖር ሲጓጓ ለማየት የፊቱን
ግን ሳይወድ ይሄዳል ሳይደርስ ምኞቱ
ሌላው ተዘጋጅቶ ሲጠባበቅ ቀኑን
ከርሞ ይፈተናል እያለመ ሞቱን
ኦ! ምን አለፋኝ መልሱ ከጠፋኝ
እሱ አይሳሳት ሁሉን በምክንያት
የኔም ዓይን አይቷል እሱ ያበራዉ
ሰሪ አይበልጥም ወይ ኦ ከተሰራው

ሰርቆ ለበላ ይበዛለታል
የታመነው አጥቶ ይንከራተታል
ለሚገባው ምነው ቢሆንለት ቢሳካለት አሃ
ለሚያምታታው ምነው ቢታይበት ቢቀጣበት አሃ
በጽናት ሲታገል ልልፋ እስኪያልፍ እያለ
ሳያልፍለት ያልፋል እንደተቃጠለ
ሌላው ግን ሳይተጋ ሳይጥር እንደደላው
ተስማምቶት ይኖራል አንድ ቀን ሳይከፋው
ኦ! ምን አለፋኝ መልሱ ከጠፋኝ
እሱ አይሳሳት ሁሉን በምክንያት
የኔም ዓይን አይቷል እሱ ያበራው
ሰሪ አይበልጥብኝ ኦ ከተሰራው
የኔም ዓይን አይቷል
የኔም ዓይን አአአይ አአአይ
የኔም ዓይን አይቷል
የኔም ዓይን
የኔም ዓይን አይቷል
የኔም ዓይን አአአይ አአአይ
የኔም ዓይን አይቷል
የኔም ዓይን
የኔም ዓይን አይቷል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists