Kishore Kumar Hits

tewodros tadesse - Emeye Ethiopia lyrics

Artist: tewodros tadesse

album: Emeye Ethiopia


እምዬ ኢትዮጵያ ይመርልሽ ሰብሉ
አውድማው ጎተራው ይሁንልሽ ሙሉ
በቸር ውሎ ይደር ጋራ ሸንተረርሽ ወንዛወንዝሽ ሁሉ
ይመስክር አካሌ ጉያሽ ያደረጀው
የእናትነት ጣምሽ ውለታሽ ያበጀው
በማጀትሽ ወተት በጤፍሽ እንጀራ
በማር በወለላ በጓሮ ሸንኮራ
ብድር አለብኝ ልክፈልና ልኩራ
ክብርሽ ከፍ ይበል ከሰላምሽ ጋራ
የወለደኝ ምጥሽ በቸር ዉሎ ይደር
ያሳደገኝ ቀዬሽ በቸር ዉሎይደር
ወንዝና ጅረትሽ በቸር ዉሎ ይደር
ጫካውና ደንሽ በቸር ዉሎ ይደር
አውድማና ማሳሽ በቸር ዉሎ ይደር
በቸር ውሎ ይደር
በቸር ዉሎ ይደር
በቸር ዉሎ ይደር ዙሪያው በቸር ዉሎይደር
በቸር ዉሎ ይደር ያሳደገኝ መንደር በቸር ዉሎይደር
እምዬ ኢትዮጵያ ይመርልሽ ሰብሉ
አውድማው ጎተራው ይሁንልሽ ሙሉ
በቸር ውሎ ይደር ጋራ ሸንተረርሽ ወንዛወንዝሽ ሁሉ
ያበቀለኝ ቀዬ የተወለድኩበት
ያበብኩበት ምድርሽ ባካል ያሸትኩበት
ሜዳውና መስኩ የፈነደኩበት
ያደኩበት ወንዝሽ የተራጨሁበት
ክፉም አልስማ ክፉም አልይበት
ሰላም ደምኖ ሰላም ይዝነብበት
የእናት ያባቴ አገር በቸር ዉሎ ይደር
የወገኔ ተገን በቸር ዉሎ ይደር
የትውልዴ መድን በቸር ዉሎ ይደር
አፈሩም ሰፈሩም በቸር ይደር
ዓየሩም ባሕሩም በቸር ይደር
በቸር ውሎ ይደር
በቸር ዉሎ ይደር በቸር ዉሎ ይደር
ዙሪያው በቸር ዉሎ ይደር
በቸር ዉሎ ይደር ያሳደገኝ መንደር
በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ዉሎ ይደር
ያደኩበት አገር
በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ይደር ያሳደገኝ መንደር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists