Kishore Kumar Hits

tewodros tadesse - Bemela Besebeb lyrics

Artist: tewodros tadesse

album: Emeye Ethiopia


በመላ በሰበብ
በዘዴ አማሃኝተሽ
በመላ በሰበብ
በዘዴ አማሃኝተሽ
ካላጣሽው ወዳጅ ከኔ ተለይተሽ
የአመልሽን ጉድ ጉድ
ትያለሽ እንዲያ እንዲያ
የአመልሽን ጉድ ጉድ
ትያለሽ እንዲያ እንዲያ
ከዚህ የተለየ ምን አገኘሽ ወዲያ
አይርታሽ ፈገግታ
አያሳሳሽ ከንፈር
አይርታሽ ፈገግታ
አያሳሳሽ ከንፈር
ሰውነት ሸክላ ነው ይበላዋል አፈር
ተሰውረሽ አትሂጅ
ሰው እንደበደለሽ
ተሰውረሽ አትሂጅ
ሰው እንደበደለሽ
ለሳቅ ለጨዋታ እዚ ምን ጎደለሽ
ለሳቅ ለጨዋታ
እዚ ምን ጎደለሽ
አንቺ ሰው ለመንገድ
ትሽቀረቀሪያለሽ
አንቺ ሰው ለመንገድ ትሽቀረቀሪያለሽ
ተይ የትም አትሂጂ የትም ትቀሪያለሽ
ካላጣሽው ፍቅር
ካልጠፋ ወዳጅ
ካላጣሽው ፍቅር
ካልጠፋ ወዳጅ
ሰው ገፍተሽ ሰው ጥለሽ
ሰው ገለሽ አትሂጂ
አትመሪ አልልም
ይመርብሽ በጣም
አትመሪ አልልም ይመርብሽ በጣም
ስትሄጅ ካላጣሽው የመታመንን ጣዕም
ያጠለቅሽው ቀሚስ
የለበስሽው ሸማ
ያጠለቅሽው ቀሚስ የለበስሽው ሸማ
ከላይም ከታችም ከገላሽ ተስማማ
ከላይም ከታችም
ከገላሽ ተስማማ
የኔው እሹሩሩ
የኔው ማቀናጣት
የኔው እሹሩሩ የኔው ማቀናጣት
ይሄው መንገድ ጥሎ አበቃኝ ለማጣት
ጤንነትሽን እንጂ
የምለምንልሽ
ጤንነትሽን እንጂ የምለምንልሽ
ከንግዲህስ ላንቺ ጨርቅም አልጥልልሽ
ከንግዲህስ ላንቺ
ጨርቅም አልጥልልሽ
ከንግዲህስ ላንቺ
ጨርቅም አልጥልልሽ
ከንግዲህስ ላንቺ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists