Kishore Kumar Hits

tewodros tadesse - Bemewadedachin lyrics

Artist: tewodros tadesse

album: Emeye Ethiopia


በመዋደዳች ስንቱን ችግር አየን
ለፍቅር ባደርን ስንቱን ፈተና አየን
ሀሜተኛም በአፉ ላይበትን ላይለየን
እንዳው ባሉባልታ በክፋት በሀሜት እያደባ አጋየን
ቢመች አመላችን ሰክኖ
ቢችላቸው እየለሰለሰ መሬት ቢሆናቸው
ማረሻ ሞፈሩን ተቸግረው ገጥመው
ቀንበር ሲያበጁልን ብዙ ጊዜ ደክመው
ሊያጣምዱን መጡ ቀንበር ተሸክመው
ሳይዙ ማስጠጋት ሳያርሙ ማገድ
ሳይጨብጡ መዝራት ሳያርሙ ማጨድ
እሄም ስራ ሆኖ ሀሜትን መፈትፈት
እንደሸት ሰመመን ኑሮን መከፋፈል
ሊበትኑን ካሉ ሊለዩን በወንፈል
መውደዴ የትም ቢወራ
ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
ሀሜኛ ቤትም አይሰራ
ተንኮልም ፍሬ አያፈራ
መውደዴ የትም ቢወራ
ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
ለተንኮል ሁሉም ቢዳዳ
ሀሜትም ያልቃል በጐዳ
በመዋደዳች ስንቱን ችግር አየን
ለፍቅር ባደርን ስንቱን ፈተና አየን
ሀሜተኛም በአፉ ላይበትን ላይለየን
እንዳው ባሉባልታ በክፋት በሀሜት እያደባ አጋየን
ይሁን ይሁን ብለው ቢነሱ ለሀሜት
ያረባ ዝማሬ መች ይነካል ስሜት
ሳይተከል እሸት ሳይታረም ፍሬ
ይሰምራል እያሉ ከነገ ከዛሬ
አጥፍተዋል ብዙ በፍቅርሽ በፍቅሬ
ሲወራ ሲናፈስ ሀሜት ቢታክትም
እህ ብለሽ ተይው አፍ አይመከትም
የኔም ባንቺ ሊቀር የንችንም ልችለው
ምነው ሰውን ሁሉ ጭንቅ ጥብብ አለው
አይወድቅም አይፈርስም ለኛ ካለው
መውደዴ የትም ቢወራ
ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
ሀሜኛ ቤትም አይሰራ
ተንኮልም ፍሬ አያፈራ
መውደዴ የትም ቢወራ
ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
ለተንኮል ሁሉም ቢዳዳ
ሀሜትም ያልቃል በጐዳ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists