Kishore Kumar Hits

tewodros tadesse - Ayeqerm Andsew lyrics

Artist: tewodros tadesse

album: Emeye Ethiopia


የጎኔ ባላ ማገር
ስላንቺስ ምን ልናገር
አይጎልም
አያልቅም
እንጀራሽም ሲጋገር
የጎኔ ባላ ማገር
ስላንቺስ ምን ልናገር
አይቀልም
አይሳሳም
እንጎቻሽም ሲጋገር
ከደሜ
የተገኘሽው ትርፌ ግምቴ
ያኮራል
ይሞቃል ባንቺ ይደምቃል ቤቴ
አልጥልሽም
አልንቅሽም
ካፈራሽ ጉልበቴ
ከራቀ
ከቀለለልኝ ስጋት ትካዜ
ካለልኝ
ከቀናኝ ኑሮ ባንቺው ማዘዜ
ያዝልቅልኝ ያክርምልኝ
ልደሰት በወዜ
ምኞቴን ከመጠንኩት
እንደራስ ካደረግኩት
ከበቃሁስ ለጉርሴ
እንዳቅም እንደኪሴ
አይቀርም እንደሰው አንጀቴን ማራሴ
አንጀቴን ማራሴ
ከሰው ፊት ከረመጡ
ከማለቅ ከመቅበጡ
ሰው ልብን ከታደለ
እራስን መቻል ካለ
ኑሮም መከታው ነው ከተስተካከለ
ከተስተካከለ
የጎኔ ባላ ማገር
ስላንቺስ ምን ልናገር
አይጎልም
አያልቅም
እንጀራሽም ሲጋገር
የጎኔ ባላ ማገር
ስላንቺስ ምን ልናገር
አይቀልም
አይሳሳም
እንጎቻሽም ሲጋገር
ሰው ነጥቆም
ከስንፈት ወድቆ ካልከፋ ስሙ
እምሽክሽክ
ብሎም ካልቀረ ተሰብሮ ቅስሙ
እጁ አይነጥፍም
ክንዱ አይመክንም
ከለፋስ እንዳቅሙ
ከደስታው
ከኑሮውም ኑሮው የጎደለበት
የከፋው
አግኝቶም ማጣት ያንዣበበት
ያገግማል ወረቱ አልቆ
ቀን የጨለመበት
ለተራው ለፈረቃው
ቢከታተል ሰቆቃው
ሰው ቅስሙን ሳይባበር
ስራን ቢያይ እንደክብር
በምድር ያፈራው ስም አይገባም መቃብር
አይገባም መቃብር
በወዙም እያደረ
ቅሪቱን ከቋጠረ
አዙሮም ካስተዋለ
መከራን ያልፋል ካለ
ቢቀጥንም አንገት ነው እራስን ከቻለ
እራስን ከቻለ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists