Kishore Kumar Hits

tewodros tadesse - Beketemaw Bemndru lyrics

Artist: tewodros tadesse

album: Emeye Ethiopia


በከተማዉ በመንደሩ
በአካባቢው በሀገሩ
ሆዴ ነይልኝ
ሆዴ ነይልኝ
ያላንቺም የለኝ
ሆዴ ነይልኝ
ሆዴ ነይልኝ
ያላንቺም የለኝ
እንክርዳድ በብርሃን የተለቀመልሽ
ገለባዉ በሌባ የተበጠረልሽ
ቀን ከሌት አስደዉሮ ለዉበት የወጠነሽ
ሲያወጣ ሲያወርድ ዉሎ
እንዴት ነው የከሸነሽ
የጥበብ ወሰኑ ነሽ
እንከን ያልጣለብሽ
ለአመል ለመዉቀሻ
ስበብ የታጣብሽ
ለጥፋት መጥቀሻ
አምላክ በቀን ጀምሮ ቅን አርጎም የጨረስሽ
በፅንነት ገንብቶ በዉበት የጨረሰሽ
በምን ቀን ነዉ ያነፀሽ
ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን
ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን
ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ
ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ
አንቺን አለ ካገር ከከተማው
በከተማው በመንደሩ
በአካባቢው በሀገሩ
ሆዴ ነይልኝ
ሆዴ ነይልኝ
ያላንችም የለኝ
በከተማው በመንደሩ
በአካባቢው በሀገሩ
ሆዴ ነይልኝ
ሆዴ ነይልኝ
ያላንችም የለኝ
ከንተርታ መንፈሴ
አይቶ ተመልክቶ
ጭንቀቴን ሊመልስ
በጥበብ መክቶ
ሊያፅናናኝ ነዉ መሰለኝ
ሀዘኔም ገርበብ አለ
ለፍቅር ብድር ሰጠኝ
ዉለታን በኔ ዋለ
አንቺን እያስከተለ
ችግር በቃ ብሎ
ፊቱን ከመለሰ
የኔም ብቸኘነት
ግምቡ ከፈረሰ
አንቺን ከፍሎ ከካሰኝ አምላክ ጎኔን ከረዳዉ
ተንጎራደጂ ከእልፍኙ በይ ከጓዳዉ
ላንቺዉ ነዉ ቤቴ የፀዳዉ
ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን
ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን
ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ
ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ
አንቺን አለ ካገር ከከተማው
ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን
ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን
ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ
ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ
አንቺን አለ ካገር ከከተማው
ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን
ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን
ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ
ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ
አንቺን አለኝ ካገር ከከተማው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists