Kishore Kumar Hits

tewodros tadesse - Sew Mamen lyrics

Artist: tewodros tadesse

album: Emeye Ethiopia


ደህና ሰንብት ብዬ ውለታዬን ልሸኘው
አብሮ መብላትንም አየሁት ስመኘው
እንግዲህስ ጥሎኛል ሰው ማመን
ዳግመኛም እንዳልቃኘው
ደህና ሁን እያልኩኝ ማመንን ልሸኘው
ሀዘን ያልፋል ብዬስ መልሼ አልቃኘው
አልሆንልህ ብሎኛል ሰው ማግኘት
ብጓጓለት ብመኘው
ቻልልኝ እያልኩት አንጀቴን
ከመጨነቅ ላውጣው
ለሰው መራራት ነው እያደር
ቅርሱን የሚያሳጣው
ያስጠቃው ያስቀጣው
እንግዲህስ እጄን አንስቼ
ምን ልቋደስበት
ሲያገኝ ለሰው ለሰው እያለኝ
እያጎረስኩበት ከተነከስኩበት
ይቅር የኔስ ማመን አለበጀም
አልቆየም ከቦታው
ለሰው የደገስኩት ደግነት
ዋንጫና ገበታው
ተሰብሯል እውነታው
አንጀቴን አየሁት
ሆዴንም ታዘብኩት
የከዳን ለመርሳት
ይችላል እያልኩት
አይጨክን ያለ ሰው አይበላ
አንጀቴ እየላላ
ቢበቃኝ ባዝል ያልጠበቅኩትን
ይደርሳል ያሰብኩት
ደህና ሰንብት ብዬ ውለታዬን ልሸኘው
አብሮ መብላትንም አየሁት ስመኘው
እንግዲህስ ጥሎኛል ሰው ማመን
ዳግመኛም እንዳልቃኘው
ደህና ሁን እያልኩኝ ማመንን ልሸኘው
ሀዘን ያልፋል ብዬስ መልሼ አልቃኘው
አልሆንልህ ብሎኛል ሰው ማግኘት
ብጓጓለት ብመኘው
ወዳጅነትንም አየሁት
ካ'ንዴም ሁለት ሶስቴ
ከሰው ጋራ ልኖር እያልኩኝ
እጄን በመክፈቴ
ፈርሶብኛል ቤቴ
አብሮ መብላት ቢበጅስ
እኔን መች ረዳኝ
ችዬ አይቼ ተውኩት እያደር
ያመንኩት ሲከዳኝ
ደግነት ሲጎዳኝ
ይብቃኝ የሰው ነገር ከእንግዲህ
ጥቃቱ እስጨከነኝ
ተበድዬም ስችል ይሁን ስል
ደግሞ እያሳዘነኝ
ሰው ማመን ተሳነኝ
አንገቴን ሰበርኩት
አይኔንም ሸፈንኩት
ከእንግዲህ ሰው ማየት
ይበቃል እያልኩት
ቢመስለኝ ብጫወት ብስቅም
ሰው ሆኖኝ አያውቅም
ምን ቢያምር ፍቅሩ እስኪጠነሰስ
አይቀር ከመደርመስ
ሲደገስ ሲወጠን ቢደምቅም
ተጀምሮ አያልቅም
ሲጀመር ሲደገስ ቢደምቅም
እንደአማረ አይዘልቅም
ሲጀመር ሲደገስ ቢደምቅም
ተጀምሮ አያልቅም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists