Kishore Kumar Hits

Dawit Tsige - Etittu lyrics

Artist: Dawit Tsige

album: Yene Zema


እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሐይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱን
እትቱ ይዞት ገባ ወይ
ዛሬስ ዛሬስ ከዓይኔ ባጣሽ
ዛሬስ ድንገት በማርፈድሽ
ዛሬስ ላምባዬን አንስቼ
ወጣሁኝ ወጣሁ ልፈልግሽ
ዛሬስ ወጣሁ ልፈልግሽ
እትቱ እትቱ በረደኝ
እትቱ በቀን በፀሐይ
እትቱ ናፍቆትሽ ክረምቱን
እትቱ ይዞት ገባ ወይ
ዛሬስ ስፍስፍ አልኩኝ ባንቺ
ዛሬስ ሰውነቴም ከዳኝ
ዛሬስ በልቤ አለ ነገር
በሰው በሰው አፍ ላይዳኝ
ዛሬስ በሰው አፍ ላይዳኝ
በቀን መብራት ይዤ ተቆጠርኩ እንደ ጅል
እኔስ ባንቺ ጉዳይ ብልጠትን አልከጅል
ሳልምሽ አምሽቼ ሲናፍቅሽ ዓይኔ
አንቺን ካላገኘው መንጋቱስ ለምኔ ዋ!
የጨዋታሽ ማማር የሳቅሽ ፏፏቴ
ውሃውን አስረሳኝ ሲፈስ ወደ አንጀቴ
ወንዙ ዳር አጥምቂኝ መልክሽ ይታየኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል
በወግ ያልነኩትን ዘራፍ ሲሉት ሸሽቶ
ይታገለኝ ጀመር ፍቅርሽ ጦር አንስቶ
አንቺው ምከሪልኝ ዘንጉን ይመልሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው ሰው
አቤት አቤት አቤት አሃሃ
አቤት አቤት አቤት ሃ...
ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ
ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ
ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ ዋ...

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists