አንዲት ሴት ነበረች የቤት ሰራተኛ
ቀን ስትደክም ውላ ሌትም የማተኛ
ኑሮዋ ሆነና የአርባ ቀን እድሏ
ልጅ እያጠባች ነው የተለያት ባሏ
ላንድ ልጇ ስትል በነፃ እየሰራች
ደሞዟን ሳትል ነው ለፍታ ያሳደገች
እንደወጣ ቢቀር ያ ባሏ ያ ጎበዝ
ስትረግም ትኖራለች ያሻገረውን ወንዝ
ለራሷ ምትቀምሰው ምትልሰው ሳይኖራት
ምን ለታጠባ ነው የምትወልደው ሲሏት
ልጅ ስጦታ አይደለም ከመጣ በኃላ
ብላ ተስፋ ቆርጣ ሄደች አገር ጥላ
አገር ጥላ ጠፍታ ተሰዳ በሩቁ
ትኑር ትሙት እንኳን አንዳቸው ሳያውቁ
ስንት ዘመን አልፎ ናፍቃ ብትመለስ
ይሄው ፊት አስነሳት የታቀፈቺው ነፍስ
ምናለ ብተወው የባሏን እሮሮ
ያሻገረውን ወንዝ መርገም በንጉርጉሮ
ወንዙን አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
ካገር አገር ስትዞር ተሸክማ ጕዟን
ስንት አሳር አይታለች ለማሳደግ ልጇን
እርፍት እንኳን ሳታውቅ በነፃ እየሰራች
ወዟን አራግፋ ነው ለፍታ ያሳደገች
ታዲያ አንድ ቀን ጠዋት ማለዳ ተነስታ
ቅጠል ለቅማ መጣ ሳታርፍ እንኳ ላፍታ
ልጇን ባንቀልባ አዝላ ውሃ ልትቀዳ
ከለመደቺው ወንዝ መሸት ሲል ወርዳ
ጎንበስ ባለችበት በድካም ስሜቷ
አመለጣት ልጇ አይ እድሏ ህብቷ
ደራሽ ወሰደባት የት ገባ ፀሎቷ
የምትወደው ልጇ ሆነ የውሃ ሽታ
ምን ያደርግላታል ብታለቅስ ብትረግመው
ከውሃ ተጣልታ የትም ለማትደርሰው
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
እሷም አለቺው ብላ ጠጋ
ላንተም አለ በጋ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ ድሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
አይ ደሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ ድሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
ደሃ
አይጣላ ከውሃ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist