Kishore Kumar Hits

Dawit Tsige - Yene Zema lyrics

Artist: Dawit Tsige

album: Yene Zema


ፍቅር ነው መንገዴ ይቅርታ ነው ልምዴ
ስኖር ከእሱ በላይ ምንም ነገር አላይ

የአበቦቹም ውበት ያልፋል ብርቱም ያሉት ይሸነፋል
የሰማዩም የምድሪቱም ፍቅር ላይ ነው መሰረቱ
ፍቅር
ፍቅር
ፍቅር
ዳገት ቁልቁለቱን ተራራውን በእግሬ
የኔ ዜማ ፍቅር
አይሰለቸኝ ብጮህ ስለ ፍቅር ዞሬ
የኔ ዜማ ፍቅር
እሾህ አያስቆመኝ አይገታኝ ጋሬጣ
የኔ ዜማ ፍቅር
ሁሉን አልፈዋለሁ በፍቅር የመጣ
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

እርካታ ነው ፍቅር ፀጋው
ተከባብሮ ለሚያወጋው
ውጤት አለው ሁሉም ነገር
ሰላም ፍቅር ሲሆን ሀገር
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

ፍቅር ነው መንገዴ ይቅርታ ነው ልምዴ

ስኖር ከእሱ በላይ ምንም ነገር አላይ

በማለዳ ልነሳ በፍቅር የተነሳ
ልገስግስ ይሙላው ቀኔን ፅድቅ የፍቅር ምናኔ
ፍቅር
ፍቅር
ፍቅር

እንደ አክሱም ድንቅ ነው እንደ ላሊበላ
የኔ ዜማ ፍቅር
ከፊት የሚቀድም ያነፁት ከኋላ
የኔ ዜማ ፍቅር
ኖረውት አልፈዋል እነ ማቱሳላም
የኔ ዜማ ፍቅር
እድሜያቸው ይመስክር ያገኙትን ሰላም
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር
ራሴን ላድን ከጥላቻው
በማለዳ በመባቻው

ጣይ ሳይመጣ ልነሳና
ወደ ፍቅር ሄድኩኝ ገና
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

የኔ ዜማ ፍቅር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists