Kishore Kumar Hits

Dawit Tsige - Yene Yene lyrics

Artist: Dawit Tsige

album: Yene Zema


እኔ ምን እልሻለሁ ቃልም የለኝ
ባንቺ ሞልቶ አይቻለሁ የጎደለኝን
ሀዘኑን ያንን ዘመን ረስቼ
በፍቅርሽ ስቄ ታየሁ ፈክቼ
በልቤ ያነገስኩሽ ፈቅጄ
ኑሪልኝ የክፉ ቀን ወዳጄ

የንጋት ፀሎቴን ያልኩትን አዳምጦ (ያልኩትን አዳምጦ)
ሀሳቤን አስረሳኝ ያሰበልኝ በልጦ (ያሰበልኝ በልጦ)
ሰላሜን ሊያበዛው ሊያስውበው ዘመኔን (ሊያስውበው ዘመኔን)
ቀኝ ያውለኝ ጀመር ሰጥቶኝ ግራ ጎኔን (ሰጥቶኝ ግራ ጎኔን)
ከላይ ከአንድዬ ባልታደልሽ
ምን እሆን ነበር የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ ኧረ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ

እኔ ምን እልሻለሁ ቃልም የለኝ
ባንቺ ሞልቶ አይቻለሁ የጎደለኝን
ሀዘኑን ያንን ዘመን ረስቼ
በፍቅርሽ ስቄ ታየሁ ፈክቼ
በልቤ ያነገስኩሽ ፈቅጄ
ኑሪልኝ የክፉ ቀን ወዳጄ

እንኳን የኔ ገላ ላንቺ የተፈጠረው (ላንቺ የተፈጠረው)
ቤቴም ሰው አገኘ የሚያነጋግረው (የሚያነጋግረው)
ትርጉም ለሰጠሻት የኔን አለም ፍቺ (የኔን አለም ፍቺ)
ከፈጣሪ በታች ልበል እድሜ ላንቺ (ልበል እድሜ ላንቺ)
ከላይ ከአንድዬ ባልታደልሽ
ምን እሆን ነበር የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ ኧረ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ
የኔ የኔ ባይልሽ እንዲያው የኔ ባይልሽ.

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists